1ያህዌ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ የሚያድር ማን ነው? በተቀደሰው ኮረብታህስ የሚኖር ማን ነው?
2አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤
3በአንደበቱ የማይሸነግል ሌሎች ሰዎችን የማይጐዳ፤ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታ የማያሰራጭ
4ነውረኛውን የሚንቅ፣ ያህዌን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፡፡ ዋጋ ቢያስከፍለው እንኳ የገባውን ቃል የሚፈጽም
5ገንዘቡን በወለድ የማያበድር ንጹሕ ሰው ላይ ለመመስከር ጉቦ የማይበላ፤ እነዚህን የሚያደርግ ከቶውንም አይናወጥም፡፡