መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሞኝ በልቡ፣ «እግዚአብሔር የለም» ይላል፡፡ ብልሹዎች ናቸው፤ አስጸያፊ ተግባርም ይፈጽማሉ፡፡ መልካም የሚያደርግ አንድም የለም፡፡
2የሚያስተውል፣ እርሱንም የሚፈልግ መኖሩን ለማየት ያህዌ ከሰማይ ወደ ምድር ተመለከተ፡፡
3ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ ሁሉም ብልሹዎች ሆነዋል ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም የሚያደርግ የለም፡፡
4እነዚያ ዐመፃ የሚያደርጉ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ፣ የያህዌን ስም የማይጠሩ ሰዎች ዕውቀት የላቸውምን?
5እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና እነርሱ በፍርሃት ተርበደበዱ!
6ምንም እንኳ ያህዌ መጠጊያው ቢሆንም እናንተ ግን ድኻውን ማዋረድ ትፈልጋላችሁ፡፡
7ያህዌ ሕዝቡን ከምርኮ ሲመለስ ለእስራኤል መዳን ከጽዮን ይመጣል ያኔ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።