1ያህዌን አመስግኑ ለያህዌ አዲስ መዝሙር ዘምሩ
2በቅዱሳን ጉባኤ ምስጋናውን አቅርቡ፡፡ እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ፡፡
3ስሙን በሽብሸባ ያመስግኑ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት፡፡
4ያህዌ በሕዝቡ ደስ ይለዋል በማዳኑ ትሑታንን ያከብራቸዋል፡፡
5ቅዱሳን በድል ደስ ይበላቸው በመኝታቸውም ላይ እልል ይበሉ፡፡
6የእግዚአብሔር ምስጋና በአንደበታቸው በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፡፡
7ይህም በአሕዛብ ላይ በቀልን፣ በሕዝቦችም ላይ ፍርድን ያደርጉ ዘንድ
8ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት መሳፍንቶቻቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፡፡
9ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው፡፡ ይህ ለቅዱሳኑ ሁሉ ክብር ይሆናል፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡