1ያህዌን አመስግኑ በሰማያት ያላችሁ ያህዌን አመስግኑ በከፍታዎች ያላችሁ ያህዌን አመስግኑ፡፡
2መላእክቱ ሁሉ አመስግኑ የመላእክቱ ሰራዊት ሁሉ አመስግት፡፡
3ፀሐይና ጨረቃ አመስግት የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፡፡
4ሰማየ ሰማያት አመስግኑት ከሰማይ በላይ ያላችሁ ውሆች አመስግኑት፡፡
5እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና የያህዌን ስም ያመስግኑ፡፡
6ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው የማይሻር ሕግም ደነገገላቸው፡፡
7የባሕር ውስጥ ፍጥረትና ጥልቁ ውሃ ሁሉ ያህዌን ከምድር አመስግኑት፡፡
8እሳትና በረዶ ዐመዳይና ጭጋግ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ
9ተራሮችና ኮረብቶች፣ የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ አመስግኑ፡፡
10የዱር አራዊት፣ የቤት እንስሳት በምድር የሚርመሰመሱ ፍጥረቶችና ወፎችም ሁሉ
11የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ መሳፍንቶችና የምድር ገዦች ሁሉ ያህዌን አመስግኑ፡፡
12ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች አረጋውያንና ሕፃናት ያመስግኑት፡፡
13የእርሱ ስም ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና ክብሩም ከምድርና ከሰማያት በላይ ነውና የያህዌን ስም ያመስግኑ፡፡
14እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቶአል ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ ለእስራኤል ልጆች፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡