መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 147

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ይመስገን አምላካችንን በመዝሙር ማመስገን እንዴት መልካም ነው እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ተገቢም ነው፡፡
2ያህዌ ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል የተበተነውን የእስራኤል ሕዝብ ይሰበስባል፡፡
3ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል ቁስላቸውንም ይጠግናል፡፡
4ከዋክብቱን ይቆጥራል ለእያንዳንዳቸውም ስም ይሰጣቸዋል፡፡
5ጌታችን ታላቅ፣ ኃይሉን የሚያስፈራ ነው ማስተዋሉም አይመረመርም፡፡
6ያህዌ የተጨቆኑትን ያነሣል ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል፡፡
7ለያህዌ በምስጋና ዘምሩ ለአምላካችን በበገና ዘምሩ፡፡
8ሰማያትን በደመና ይሸፍናል በተራሮች ሣር እንዲበቅል ለምድር ዝናብ ያዘጋጃል፡፡
9ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቁራ ጫጩቶች ሲንጫጩ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል፡፡
10በፈረስ ኃይል አይደሰትም ደስታውን በሰው ጉልበት ጥንካሬ አያደርግም፡፡
11ያህዌ በሚፈሩት፣ በምሕረቱም በሚታመኑ ይደሰታል፡፡
12ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ ጽዮንም አምላክሽን አወድሺ
13እርሱ የበሮችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና በመካከልሽ ያሉ ልጆችሽንም ባርኮአል፡፡
14በድንበርሽ ውስጥ ብልጽግና አድርጐአል ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል፡፡
15ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል ቃሉም በፍጥነት ይሮጣል፡፡
16በረዶውን እንደ ባዘቶ ያነጥፈዋል ጭጋጉንም እንደ ደመና ይበትነዋል፡፡
17የበረዶውን ድንጋይ ቁልቁል ይለቃል በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን መቆም ይችላል?
18ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል ነፋሱን ያነፍሳል ውሃንም ያፈስሳል፡፡
19ቃሉን ለያዕቆብ፣ ሥርዐት ጽድቁንም ለእስራኤል ያውጃል፡፡
20ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ ይህን አላደረገም እነርሱም ፍርዱን አላወቁም፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።