1ያህዌን አመስግኑ ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን ባርኪ፡፡
2በሕይወት በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለያህዌ እዘምራለሁ፡፡
3በገዦች አትተማመኑ ማዳን በማይችል የሰው ልጅም አትመኩ፡፡
4የሰው እስትንፋስ ሲያቆም ወደ መሬት ይመለሳል፡፡ ያን ጊዜ ዕቅዱ እንዳልነበረ ይሆናል፡፡
5ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ ተስፋውም ያህዌ የሆነለት ሰው የተባረከ ነው፡፡
6ሰማይና ምድርን፣ ባሕርንና በውስጡ ያሉትንም የፈጠረ ያህዌ
7ለተጨቆኑት የሚፈርድ፣ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፡፡ ያህዌ እስረኞችን ነጻ ያወጣል፡፡
8ያህዌ የዕውራን ዐይን ይከፍታል፡፡ ያህዌ የተዋረዱን ከፍ ያደርጋል፡፡ ያህዌ ጻድቃንን ይወዳል፡፡
9ያህዌ መጻተኞን በምድር ይጠብቃል ደኸ አደጐችንና መበለቶችን ይደግፋል፡፡ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል፡፡
10ያህዌ ለዘላለም ይነግሣል ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡