1እጆቼን ለጦርነት ጣቶቼንም ለውጊያ የሚያሠለጥን ዐለቴ ያህዌ ይባረክ፡፡
2አንተ መታመኛዬና መጠጊያዬ ነህ ጽኑ ዐምባዬና ታዳጊዬ የምከለልበት ጋሻዬም ነህ ሕዝቦችን ከእግሬ በታች የምታስገዛልኝም አንተ ነህ፡፡
3ያህዌ ሆይ፣ ይህን ያህል የምትንከባከበው ሰው ምን ስለሆነ ነው? ይህን ያህል የምታስብለት የሰው ልጅስ ምንድነው?
4ሰው እንደ እስትንፋስ ነው ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል፡፡
5ያህዌ ሆይ፣ ሰማያትን ሰንጥቀህ ውረድ ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስሳቸው፡፡
6የመብረቅ ብልጭታ ልከህ ጠላቶቼን በትናቸው ፍላጻህን ሰድደህ ግራ አጋባቸው፡፡
7ከላይ እጅህን ሰደህ ከብዙ ውሆች፣ ከባዕድ ሰዎችም እጅ ታደገኝ፡፡
8አንደበታቸው ሐሰት ይናገራል ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት፡፡
9አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ ዐሥር አውታር ባለው በገና ምስጋና አቀርብልሃለሁ፡፡
10አንተ ነገሥታትን ድልን ታጐናጽፋቸዋለህ አገልጋይህ ዳዊትንም ከስለታም ሰይፍ ትታደገዋለህ፡፡
11አንደበታቸው ሐሰት ከሚናገር ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው ከባዕዳን እጅ ታደገኝ፡፡
12ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ፡፡
13ጐተራዎቻችን በተለያዩ የእህል ዐይነቶች የተሞሉ ይሁኑ፡፡ በመስኮቻችን የተሰማሩ በጐች እስከ ሺህ ይወለዱ፣ እስከ ዐሥር ሺህ ይባዙ፡፡
14ከብቶቻችን ወላድ ይሁኑ፡፡ አይጨንግፉ አይጥፉ ቅሮቻችን በማንም አይደፈሩ እኛም በምርኮ አንወሰድ፡፡ በአደባባዮቻችን ጩኸት አይሰማ፡፡
15እንዲህ የሚሆንለት ሕዝብ የተባረከ ነው ያህዌ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ የተባረከ ነው፡፡