1ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ ልመናዬንም አድምጥ፡፡ በታማኝነትህና በጽድቅህ ሰምተህ መልስልኝ፡፡
2በአንተ ፊት ማንም ጻድቅ አይደለምና ከባርያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ፡፡
3ጠላት ነፍሴን አሳደዳት ገፍትሮም ወደ መሬት ጣለኝ፡፡ ቀደም ብለው እንደ ሞቱ ሰዎች በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል፡፡
4ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ልቤም ተስፋ ቆረጠ፡፡
5የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ አንተ ያደረግኸውንም አውጠነጠንሁ፡፡
6በጸሎት እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ እንደ ደረቀች ምድር ነፍሴ አንተን ተጠማች፡፡ ሴላ
7ያህዌ ሆይ፣ መንፈሴ ዝሎአልና ፈጥነህ ስማኝ፡፡ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ እንዳልሆን ፊትህንም ከእኔ አትሰውር፡፡
8በአንተ ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፡፡ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ፡፡
9ያህዌ ሆይ፣ አንተን መሸሸጊያ አድርጌአለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ፡፡
10አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ማድረግ አስተምረኝ፡፡ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ፡፡
11ያህዌ ሆይ፣ ስለ ስምህ በሕይወት ጠብቀኝ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት፡፡
12ከታማኝነትሀ የተነሣ ጠላቶቼን አጥፋቸው እኔ ባርያህ ነንና የሕይወቴን ጠላቶች ደምስሳቸው፡፡