መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 142

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ድምፄን ከፍ አድርጌ እንዲረዳኝ ወደ ያህዌ እጮኻለሁ ድምፄን ከፍ አድርጌ እንዲምረኝ ልመናየን ወደ ያህዌ አቀርባለሁ፡፡
2ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ ችግሬንም እነግረዋለሁ፡፡
3መንፈሴ በውስጤ ሲዝል አንተ መንገዴን ታውቃለህ፤ መተላለፊያ መንገዴ ላይ በስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ፡፡
4ወደ ቀኜ ብመለከት የሚያስብልኝ ሰው አጣሁ ማምለጫም የለኝም ለሕይወቴም ደንታ ያለው የለም፡፡
5ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እጮኻለሁ «አንተ መጠጊያዬ ነህ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ» እላለሁ፡፡
6እጅግ ተስፋ ቆርጫለሁና ጩኸቴን ስማ ከእኔ ይበልጥ ብርቱ ስለሆኑ ከአሳዶጆቼ አድነኝ፡፡
7ስምህን እንዳመሰግን ነፍሴን ከእስር ቤት አውጣት፡፡ ለእኔ ያደረግኸውን መልካም ነገር ሲመለከቱ ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።