መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 141

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ ፈጥነህ ድረስልኝ ወደ አንተ ስጣራ ድምፄን ስማ
2ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ይሁንልኝ ወደ አንተ ያነሣሁት እጄም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይቆጠርልኝ፡፡
3ያህዌ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አኑር የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ
4ክፉ ለማድረግ ከመመኘትና ከክፉ አድራጊዎች ጋር ከመተባበር፣ የድግሳቸውም ተካፋይ ከመሆን ጠብቀኝ፡፡
5ጻድቅ ሰው ቢቀጣኝ ለእኔ በጐነት ነው፤ እርሱ ቢገሥጸኝ ራሴን እንደሚቀባ ዘይት ነው እኔ ራሴም ይህን እንቢ አልልም፡፡ ጸሎቴ ግን ሁሌም በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፡፡
6መሪዎቻቸው ከገደል ጫፍ ቁልቁል ይወርወሩ ቃሌ እውነት መሆኗንም ይሰማሉ፡፡
7ደግሞም፣ «ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣ እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል አፋፍ ላይ ተበታተነ» ይላሉ፡፡
8ጌታ፣ ያህዌ ሆይ፣ ዐይኖቼ ወደ አንተ ይመለከታሉ መጠጊያዬ አንተ ነህ፤ ከእንግዲህ ነፍሴን አትተዋት፡፡
9ከዘረጉብኝ ወጥመድ ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ፡፡
10እኔ በደኅና ሳመልጥ ክፉዎች በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።