1ያህዌ ሆይ፣ ከክፉ ሰዎች አድነኝ ከዐመፀኞችም ጠብቀኝ፡፡
2እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ፡፡
3ምላሳቸው እንደ እባብ ይነድፋል የእፉኝትም መርዝ በከንፈራቸው አለ፡፡ ሴላ
4ያህዌ ሆይ፣ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ መትተው ሊጥሉኝ ከሚፈልጉ ዐመፀኛ ሰዎች አድነኝ፡፡
5ትዕቢተኞች በስውር ወጥመድ ዘርግተውብኛል የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ በመንገዴም አሽክላ አኖሩ፡፡ ሴላ
6እኔም ያህዌን፣ «አንተ አምላኬ ነህ እንድትምረኝ የማቀርበውን ጩኸት ስማ» እለዋለሁ፡፡
7ያህዌ ሆይ፣ እኔን ለማዳን ብርቱ ነህ በጦርነት ቀን ራሴን ከለልህ፡፡
8ያህዌ ሆይ፣ የክፉዎች ምኞት አይሳካ ሤራቸውም አይከናወን፡፡
9ዙሪያዬን የከበቡኝ ራሳቸውን ቀና ቀና አደረጉ የገዛ ከንፈራቸው ሸፍጥ ይዋጣቸው፡፡
10የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ እሳት ውስጥ ጣላቸው ዳግመኛም እንዳይነሡ ማጥ ወዳለበት ጉድጓድ ይውደቁ፡፡
11ምላሰኛ በምድሪቱ ጸንቶ አይኑር ዐመፀኛውን ክፋት አሳድዶ ያጥፋውቨ
12ያህዌ ለተበደሉ እንደሚፈርድ ለችግረኛውም ፍትሕ እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ፡፡
13ጻድቃን በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ፡፡