መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 139

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ መረመርኸኝ፤ ደግሞም ዐወቅኸኝ፡፡
2አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቅ ትረዳለህ፡፡
3መሄድ መተኛቴን በሚገባ ታውቃለህ መንገዶቼንም ሁሉ ዐውቀሃቸዋል
4ገና ቃል ከአንደበቴ ሳይወጣ ያህዌ ሆይ፣ ፈጽመህ ታውቃለህ፡፡
5አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ እጅህንም በላዬ አደረግህ፡፡
6እንዲህ ያለው ዕውቀት እጅግ ጥልቅ ነው ከእኔም ማስተዋል በላይ ነው፡፡
7ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ፡፡
8ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ መኝታዬን በሲኦል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ፡፡
9በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር እስከ ባሕሩ መጨረሻ ብሄድ
10በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች ቀኝ እጅህም ትይዘኛለች፡፡
11ደግሞም፣ «ጨለማው በእርግጥ ይሸፍነኛል በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ይሆናል» ብል
12ጨለማ እንኳ ለአንተ አይጨልምም ሌሊቱም እንደ ቀን ያበራል በአንተ ጨለማም ሆነ ብርሃን አንድ ናቸው፡፡
13አንተ የውስጥ ሰውነቴን ፈጥረሃል በእናቴ ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ፡፡
14ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው ነፍሴም ይህን በሚገባ ታውቃለች፡፡
15እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፡፡ በምድር ጥልቅ ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ
16በእናቴ ማሕፀን እያለሁ አየኸኝ፡፡ ገና አንዳቸውም ወደ መኖር ሳይመጡ ለእኔ የተወሰኑልኝ ዘመኖች በመጽሐፍህ ተጻፉ፡፡
17አምላኬ ሆይ፣ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ግሩም ነው! ቁጥሩስ ምንኛ የበዛ ነው!
18ልቁጠራቸው ብል ከአሸዋ ቁጥር ይበልጣሉ ተኛሁ ነቃሁም፤ ያም ሆኖ ግን አሁንም ከአንተው ጋር ነኝ፡፡
19አምላክ ሆይ፣ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት! ደም የጠማችሁ ዐመፀኞች ከእኔ ራቁ፡፡
20እነርሱ በአንተም ላይ ክፉ ይናገራሉ በጠላትነትም ስምህን በክፉ ያጠፋሉ፡፡
21ያህዌ ሆይ፣ የሚጠሉህን አልጠላሁምን? በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልተጸየፍሁምን?
22በፍጹም ጥላቻ ጠልቻቸዋለሁ እነርሱም ባላጋራዎቼ ሆነዋል፡፡
23እግዚአብሔር ሆይ፣ መርምረኝ ልቤንም ዕወቅ ፈትነኝ ሐሳቤንም ዕወቅ፡፡
24በእኔ ውስጥ የዐመፅ መንገድ ቢኖር እይ በዘላለምም መንገድ ምራኝ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።