መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ? ፊትህን ከእኔ የምትሰውረውስ እስከመቼ ድረስ ነው?
2በስጋት የምኖረው ልቤስ ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው? ጠላቴ እኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ነው?
3ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ ወደ እኔ ተመልከት መልስልኝም!
4የሞት እንቅልፍ እንዳይወስደኝ ዐይኖቼን አብራ፡፡ ጠላቴ፣ «አሸነፍሁት» እንዳይል ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ፡፡
5እኔ ግን ወሰን በሌለው ፍቅርህ እተማመናለሁ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል፡፡
6ቸርነቱ በዝቶልኛልና ለያህዌ እዘምራለሁ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።