1በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ በአማልክትም ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ፡፡
2ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ ቃልህንና ስምህን ከሁሉ በላይ ከፍ አደረግህ፡፡
3በጠራሁህ ቀን መለስህልኝ ነፍሴን በማጽናናት አደፋፈርሃት፡፡
4ያህዌ ሆይ፣ የአፍህን ቃል ሲሰሙ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፡፡
5የያህዌ ክብር ታላቅ ነውና ስለ ያህዌ ሥራ ይዘምራሉ፡፡
6ያህዌ እጅግ ከፍ ያለ ቢሆንም፣ ዝቅ ያሉትንም ይመለከታል ትዕቢተኞችን ግን ገና ከሩቅ ያውቃቸዋል፡፡
7በአደጋ መካከል ብሄድ እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ፡፡ እጅህን ዘርግተህ ከጠላቶቼ ቁጣ ታወጣኛለህ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ፡፡
8ያህዌ እስከ መጨረሻ ከእኔ ጋር ነህ ያህዌ ሆይ፣ ምሕረትህ ለዘላለም ነው፡፡ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል፡፡