መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 137

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን፡፡
2እዚያ በገናዎቻችንን በአኻያ ዛፎች ላይ ሰቀልን፡፡
3የማረኩን ሰዎች እንድንዘምርላቸው ጠየቁን ሲያፌዙብን የነበሩት የደስታ ዜማ ፈለጉብን፣ «እስቲ ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን» አሉን፡፡
4የያህዌን መዝሙር እንዴት ብለን በባዕድ ምድር እንዘምራለን?
5ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ብረሳሽ ቀኝ እኔ ይክዳኝ፡፡
6አንቺን ሳላስታውስ፣ ደስ ከሚያሰኘኝ ነገር ሁሉ በላይ ሳላደርግሽ ብቀር ምላሴ ከትናጋዬ ትጣበቅ፡፡
7ያህዌ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፡፡ እነርሱ፣ «አፍርሷት፣ ጨርሳችሁ አፍርሷት!» አሉ፡፡
8የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ እኛ ላይ ስላደረግሺው ድርጊት ብዙም ሳይቆይ፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ የተባረከ ነው
9ሕፃናቶችሽን ዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ እርሱ የተመሰገነ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።