1ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
2የአማልክትን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
3የጌቶችን ጌታ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
4ብቻውን ታላላቅ ተአምራት ያደረገውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
5በጥበብ ሰማያትን የሠራ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
6ምድርን ውሃ ላይ የዘረጋ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
7ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
8ፀሐይ በቀን እንዲገዛ ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
9ጨረቃና ከዋክብት ሌሊት እንዲገዙ ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
10የግብፅን በኩር የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
11እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
12በብርቱ እጅ፣ በተዘረጋችም ክንድ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
13ቀይ ባሕርን የከፈለውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
14እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
15ፈርዖንና ሰራዊቱን ቀይ ባሕር ውስጥ ያሰጠመ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
16ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
17ታላላቅ ነገሥታትን የገደለውን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
18ኃያላን ነገሥታትን የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
19የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎንን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
20የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
21ምድራቸውን ርስት አድርጐ የሰጠ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
22ለባርያው ለእስራኤል ርስት አድርጐ የሰጠ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
23በውርደታች ያሰበን፣ የረዳንም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
24በጠላቶቻችን ላይ ድል የሰጠን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
25ለፍጡር ሁሉ ምግብ የሚሰጥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
26የሰማይን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡