1ያህዌን አመስግኑ የያህዌን ስም ወድሱ፤ እናንት የያህዌ አገልጋዮች አመስግኑት፡፡
2በያህዌ ቤት በአምላካችንም ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት፡፡
3መልካም ነውና ያህዌን አመስግኑ ደስ የሚያሰኝ ነውና ለስሙ ዘምሩ፡፡
4ያህዌ ያዕቆብን ለራሱ፣ እስራኤልም ርስቱ እንዲሆን መርጦአልና፡፡
5ያህዌ ታላቅ መሆኑን፣ ጌታችንም ከአማልክት በላይ መሆን ዐውቃለሁ፡፡
6በሰማይም ሆነ በምድር በባሕርና በጥልቅ ውቅያኖስ ያህዌ የወደደውን ያደርጋል፡፡
7እርሱ ደመናትን ከሩቅ ቦታ ያመጣል ከዝናብ ጋር መብረቅ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል፡፡
8ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ የግብፃውያንን በኩር ገደለ፡፡
9ግብፅ ሆይ፣ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣ በመካከልሽም ምልክቶችንና ድንቆችን አደረገ፡፡
10ብዙ ሕዝቦች መታ ኃያላን ነገሥታት ገደለ፡፡
11የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎንን የባሰን ንጉሥ ዐግን የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፡፡
12ምድራቸውንም ለሕዝቡ ለእስራኤል ርስት አድርጐ ሰጠ፡፡
13ያህዌ ሆይ፣ ስምህ ዘላለማዊ ነው መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል፡፡
14ያህዌ ለሕዝቡ ይፈርዳልና ለአገልጋዮቹም ይራራልና፡፡
15የአሕዛብ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ በሰው እጅ የተሠሩ ናቸው
16አፍ አላቸው አይናገሩም ዐይን አላቸው አያዩም፡፡
17ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ በአፋቸውም እስትንፋስ የለም፡፡
18የሚሠሩዋቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ፡፡
19የእስራኤል ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ የአሮን ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ፡፡
20የሌዊ ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ ያህዌን የምትፈሩ ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ፡፡
21በኢየሩሳሌም የሚኖር ያህዌ ከጽዮን ይባረክ ያህዌን አመስግኑ፡፡