መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ ደግ ሰው የለምና አንተው እርዳኝ ከሰው ዘር መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም፡፡
2እያንዳንዱ ሰው ለባልንጀራው ባዶ ቃላት ይናገራል በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራል፡፡
3ሸንጋይ ከናፍርቶችንና በትምክህት የሚናገሩ አንደበቶችን ያህዌ ያጥፋ፡፡
4እነዚህም፣ «በአንደበታችን እንበረታለን የምንናገረውንስ ማን ማስተባበል ይችላል?» የሚሉ ናቸው፡፡
5«ስለ ድኾች መከራ፣ ስለ ችግረኞች ጩኸት ያህዌ አሁን እነሣለሁ፤ የናፈቁትንም ሰላም እሰጣቸዋለሁ» ይላል፡፡
6የያህዌ ቃሎች የነጹ ቃሎች ናቸው በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው፡፡
7ያህዌ ሆይ፣ አንተ ትጠብቀናለህ ከዚህ ዐመፀኛ ትውልድ ለዘላለም ጻድቃንን ትጠብቃለህ፡፡
8በሰው ልጆች መካከል ክፋት በገነነበት ጊዜ ዐመፀኞች እንዳሻቸው በየቦታው ይዘራሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።