1በያህዌ የሚተማመኑ ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር የጽዮን ተራራ ናቸው፡፡
2ተራሮች ኢየሩሳሌምን እንደ ከበቧት ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ያህዌም በሕዝቡ ዙሪያ ነው፡፡
3ጻድቁ ክፉ እንዳያደርግ የዐመፃ በትረ መንግሥት የጻድቃንን ምድር አይግዛ፡፡
4ያህዌ ሆይ፣ መልካም ለሆኑ፣ ልባቸውም ቀና ለሆኑት መልካም አድርግ፡፡
5ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን ያህዌ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያጠፋቸዋል፡፡ ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን፡፡