1ያህዌ የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ሕልም እንጂ፣ እውን አልመሰለንም፡፡
2በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በዝማሬ ተሞላ፡፡ በዚያ ጊዜ በሕዝቦች መካከል፣ «ያህዌ ታላቅ ነገር አደረገላቸው» ተባለ፡፡
3ያህዌ ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም እጅግ ደስ አለን፡፡
4ያህዌ ሆይ፣ በኔጌቭ እንዳሉ ምንጮች ምርኮአችን መልስ፡፡
5በእንባ የሚዘሩ በእልልታ ይዘራሉ
6ዘሩን ተሸክመው እያለቀሱ የተሰማሩ ነዶአቸውን ተሸክመው እልል እያሉ ይመለሳሉ፡፡