1«ያህዌ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ» ይበል እስራኤል፡፡
2ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ ያህዌ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ
3ቁጣቸው በእኛ ላይ በነደደ ጊዜ በሕይወት እያለን በዋጡን ነበር፡፡
4ጐርፍ በወሰደን፣ ውሃም በሸፈነን ነበር፡፡
5ብርቱ ማዕበልም ባሰጠመን ነበር
6በጥርሳቸው እንዲቦጫጭቁን ያልፈቀደ ያህዌ ይባረክ
7ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኝ ወጥመድ አመለጠች ወጥመዱ ተሰበረ እኛም አመለጥን፡፡
8ሰማይና ምድርን የሠራ ያህዌ ረዳታችን ነው፡፡