1ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይመጣል?
2ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከያህዌ ዘንድ ይመጣል፡፡
3እግርህ እንዲንሸራተት አይፈቅድም አንተን የሚጠብቅህም አይተኛም፡፡
4እነሆ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፉምም፡፡
5ያህዌ ይጠብቅሃል፤ ያህዌ በቀኝህ በኩል ይከልልሃል፡፡
6ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት አይጐዳህም፡፡
7ያህዌ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል እርሱ ሕይወትህንም ይጠብቃል፡፡
8ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም ያህዌ በምታደርገው ሁሉ ይጠብቅሃል፡፡