1«ወደ ያህዌ ቤት እንሂድ» ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፡፡
2ኢየሩሳሌም ሆይ፣ እግሮቻችን በደጆችሽ ውስጥ ቆመዋል፡፡
3ኢየሩሳሌም በጥንቃቄ የተገነባች ከተማ ናት!
4ለእስራኤል ምስክር ይሆን ዘንድ ነገዶች፣ የያህዌ ነገዶች ወደዚያ ይወጣሉ፡፡
5በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል፡፡
6ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፡፡ «የሚወዱሽ ሰላም ይሁንላቸው፡፡
7በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን በምሽጐችሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን፡፡»
8ስለ ወንድሞቼና ስለ ወዳጆቼ ኢየሩሳሌምን፣ «ሰላም ከአንቺ ጋር ይሁን» እላታለሁ፡፡
9ስለ አምላካችን ያህዌ ቤት መልካም እንዲሆንልሽ እሻለሁ፡፡