1በጨነቀኝ ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣራሁ እርሱም መለሰልኝ፡፡
2ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ፡፡
3እናንት አታላዮች እግዚአብሔር እንዴት ይቅጣችሁ፣ ምንስ ቢከፍላችሁ ይሻላል?
4በተሳለ የጦረኛ ቀስት በግራር ከሰል ፍም ይቀጣችኃል፡፡
5የምኖረው በሜሼክ ስለ ሆነ የነበርኩትም በቄዳር ድንኳኖች መካከል ስለ ነበር ወዮልኝ፡፡
6ሰላምን ከሚጠሉ ጋር በጣም ረጅም ጊዜ ኖርሁ፡፡
7እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፡፡ በተናገርሁ ጊዜ ግን እነርሱ ጠብ ይፈልጋሉ፡፡