መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 114

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ሲሄድ የያዕቆብም ቤት ከባዕድ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ
2ይሁዳ ቅዱስ ማደሪያው እስራኤልም ግዛቱ ሆነ፡፡
3ባሕር ዐይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ላኋው ተመለሰ፡፡
4ተራሮች እንደ አውራ በግ ፈነጩ ኮረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ፡፡
5አንተ ባሕር ምን ሆነህ ሸሸህ? አንተስ ዮርዳኖስ ለምን ወደ ኃላህ ተመለስህ?
6እናንተ ተራሮች ስለምን እንደ አውራ በግ ፈነጫችሁ? ኮረብቶችስ ለምን እንደ ጠቦት ዘለላችሁ?
7ምድር ሆይ፣ በጌታ ፊት በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፡፡
8እርሱ ዐለቱን ወደ ውሃ ኩሬ ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።