መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 113

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ይመስገን፡፡ የያህዌ አገልጋዮች ሆይ፣ የያህዌን ስም አመስግኑ፡፡
2ከአሁን እስከ ዘላለም የያህዌ ስም ይመስገን፡፡
3ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ የያህዌ ስም ይመስገን፡፡
4ያህዌ ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው፡፡
5እንደ አምላካችን እንደ ያህዌ በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?
6ራሱን ዝቅ አድርጐ በሰማይና በምድር ያሉትንስ የሚያይ ማን ነው?
7ድኻውን ከትቢያ ያነሣል ችግረኛውንም ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡
8ከመኳንንት ጋር፣ ከሕዝቡም ሹማምንት ጋር ያስቀምጠዋል፡፡
9መካኒቱን በቤት ያኖራታል ደስ የተሰኘች የልጆች እናት ያደርጋታል፡፡ ያህዌ ይመስገን!
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።