1ያህዌ ይመስገን ያህዌን የሚፈራ በትእዛዞቹም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው፡፡
2ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል የቅኖች ትውልድ ይባረካል፡፡
3ሀብትና ብልጽግና ቤቱን ይሞላል ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል፡፡
4ምሕረትና ቸርነት፣ ቅንነትንም ለሚያደርግ ደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል፡፡
5ሥራውን በትክክል የሚያከናውን፣ ለጋስና ሳይሰስት የሚያበድር ሰው መልካም ይሆንለታል፡፡
6እርሱ ከቶውንም አይናወጥምና ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል፡፡
7እምነቱን ያህዌ ላይ ያደረገ ልበ ሙሉ ስለሆነ ክፉ ወሬ አያሸብረውም፡፡
8ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው፡፡ በመጨረሻ የጠላቶቹን ውድቀት ያያል፡፡
9በልግስና ለድኾች ይሰጣል ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል፡፡ በክብር ከፍ ከፍ ይላል፡፡
10ክፉ ሰው ይህን፤ በማየት ይበሳጫል ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፡፡ የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች፡፡