መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 110

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ጌታዬን፣ «ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ» አለው፡፡
2ያህዌ ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰዳል አንተም በጠላቶችህ መካከል ትገዛለህ፡፡
3በኃይልህ ቀን ተከታዮችህ የተቀደሰ ልብስ ተጐናጽፈው በፈቃዳቸው ይከተሉሃል፡፡ ከንጋት ማሕፀን ጐልማሳነትህ እንደ ጠል ይወጣል፡፡
4«እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ» ብሎ ያህዌ ምሎአል፤ እርሱም ሐሳቡን አይለውጥም፡፡
5ጌታ በቀኝህ ነው በቁጣው ቀን ነገሥታትን ይገድላል፡፡
6በሕዝብ ላይ ይፈርዳል የጦር ሜዳዎችን ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፡፡ የብዙ አገሮችን ነገሥታት ይደመሰሳል፡፡
7መንገድ ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል ከድል በኃላ ራሱን ቀና ያደርጋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።