መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 109

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የማመሰግንህ አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበለኝ
2ክፉዎችና አታላዮች አጥቅተውኛልና በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ፡፡
3በጥላቻ ዙሪያዬን ከበቡኝ ያለ ምክንያትም በድለውኛል፡፡
4ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤ እኔ ግን ለእነርሱ እጸልያለሁ፡፡
5በመልካም ፈንታ ክፋትን በወደድኃቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል፡፡
6በእንዲህ ያለው ሰው፣ ክፉ ሰው በላዩ ሹም ከሳሽም በቀኙ ይቁም፡፡
7በተሟገተ ጊዜ ተረትቶ ይግባ ጸሎቱ እንኳ እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት፡፡
8ዕድሜው ይጠር ሹመቱን ሌላው ይውሰደው፡፡
9ልጆቹ ድኻ አደጐች ይሁኑ ሚስቱም መበለት ትሁን፡፡
10ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ ከፈረሰው ቤታቸው ይሰደዱ፡፡
11ንብረቱ ሁሉ በዕዳ ይያዝበት ለፍቶ ያገኘውን ጥሪት ባዕዳን ሰዎች ይውሰዱበት፡፡
12ማንም ሰው ደግ አይሁንለት ለድኻ አደግ ልጆቹ የሚራራላቸው አይገኝ፡፡
13ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ፡፡
14የአባቶቹ ኃጢአት በያህዌ ፊት ይታሰብ የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ፡፡
15በደላቸው ሁልጊዜ በያህዌ ፊት ይሁን የእነርሱ መታሰቢያ ግን ጨርሶ ይጥፋ፡፡
16ይህ ሰው ምሕረት ከማድረግ ይልቅ፣ ችግረኛውንና ምስኪኑን ልቡም የቆሰለውን እስከ ሞት አሳድዶአልና ያህዌ ይህን ያደርግበት
17መርገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች መባረክ አልወደደም በረከት ከእርሱ ይራቅ፡፡
18መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤ ስለዚህ መርገም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፣ እንደ ዘይትም ወደ አጥንቱ ዘለቀች፡፡
19ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው፡፡
20ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣ እኔ ላይ ክፉ ለሚናገሩ ያህዌ የሚከፍለው ይኸው ይሁን፡፡
21አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ስለ ስምህ ስትል እኔን በበጐ ተመልከተኝ፡፡
22እኔ ድኽና ችግረኛ ነኝ ልቤም በውስጤ ቆስሎአል፡፡
23እንደ ምሽት ጥላ ላልፍ ተቃርቤአለሁ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ፡፡
24በጾም ምንያት ጉልበቴ ደከመ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ መሰለ፡፡
25ለጠላቶቼ መሣለቂያ ሆንሁላቸው ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቁብኛል፡፡
26አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ርዳኝ ስለ ታማኝነትህም አድነኝ፡፡
27ያህዌ ሆይ፣ እጅህ ይህን እንዳደረገች አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ፡፡
28እነርሱ ቢራገሙ እንኳ አንተ ግን ባርከኝ እኔን ሲያጠቁኝ ይዋረዱ ባርያህ ግን ሐሤት ያደርጋል፡፡
29ባላንጣዎቼ ውርደትን እንደ ልብስ ይልበሱ እፍረትንም እንደ ሸማ ይጐናጸፉ፡፡
30በአንደበቴ ያህዌን እጅግ አመሰግለሁ በጉባኤም መካከል እባርከዋለሁ፡፡
31በእርሱ ላይ ከሚፈርዱ ለማዳን እርሱ በችግረኛው ቀኝ ይቆማልና፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።