መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 104

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ ውበትና ግርማን ለብሰሃል፡፡
2ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፡፡
3በጠፈር ላይ ካለው ውሃ በላይ ቤትህን ሠርተሃል ደመናትን ሰረገላህ አደረግህ በነፋስ ክንፎች ትሄዳለህ፡፡
4ነፋሶችን መልእክተኞቹ፣ ነበልባልንም አገልጋዮቹ አደረግ፡፡
5ምድርን መሠረት ላይ አጸና ከቶም አትናወጥም፡፡
6በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ፡፡
7በገሠጸካቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ፡፡
8በተራሮች ላይ ፈሰሱ አንተ ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ ወደ ሸለቆዎች ወረዱ፡፡
9ዳግመኛ ምድርን እንዳይሸፍኑም አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው፡፡
10ምንጮች በሸለቆው ውስጥ እንዲ ወንዞችም በተራሮች መካከል እንዲወርዱ አደረግህ፡፡
11የዱር እንስሳት ከዚያ ይጠጣሉ የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ያረካሉ፡፡
12ወንዙ ዳር ወፎች ጐጆአቸውን ይሠራሉ በቅርንጫፎቹም መካከል ይዘምራሉ፡፡
13ከላይ ከእልፍኙ ተራሮችን ያጠጣል፤ ምድርም በሥራው ፍሬ ትረካለች፡፡
14ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ ለእንስሶች ሣርን ታበቅላለህ ለሰው ልጆች ሥራ አትክልቶችን ታበቅላለህ፡፡
15ስለዚህ ልቡን ደስ የሚሰኘውን ወይን ጠጅ፣ ፊቱን የሚያበራ ዘይትና በሕይወት የሚያኖረውን እህል ያዘጋጃል፡፡
16ደግሞም የያህዌ ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች በቂ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
17በዚያ ወፎች ጐጆአቸውን ይሠራሉ ሽመላዎችም በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ያገኛሉ፡፡
18ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ ተራራ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው፡፡
19ጨረቃ የወቅቶች ምልክት እንድትሆን አደረገ ፀሐይም የምትጠልቀበትን ጊዜ ታውቃለች፡፡
20ጨለማን ፈጠርህ፤ ሌሊትም ሆነ፤ በጨለማም የዱር አውሬዎች ሁሉ ይወጣሉ፡፡
21የአንበሳ ግልግሎች ምግብ ለማግኘት ይጫኸሉ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምግባቸውን ይፈልጋሉ፡፡
22ፀሐይ በወጣች ጊዜ ሸሽተው ይሄዳሉ፤ በየመኖሪያቸው ውስጥ ይተኛሉ፡፡
23ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል እስኪመሽም ድረስ ሲሠራ ይውላል፡፡
24ያህዌ ሆይ፣ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ አደረግህ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች፡፡
25እዚያ ደግሞ ሰፊና የተንጣለለ ባሕር አለ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸውም ነፍሳት በውስጡ አሉ፡፡
26መርከቦች በላዩ ይመላለሳሉ አንተ የፈጠርኸው ሌዋታን በውስጡ ይፈነጫል፡፡
27እነዚህ ሁሉ በጊዜው ምግባቸውን እንድትሰጣቸው አንተን ተስፋ ያደርጋሉ፡፡
28በሰጠሃቸው ጊዜ አንድ ላይ ይከማቻሉ፣ እጅህንም ስትዘረጋ በመልካም ነገር ይጠግባሉ፡፡
29ፊትህን ስትሰውር፣ በጣም ይደነግጣሉ እስትንፋሳቸውን ስትወስድ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ፡፡
30መንፈስህ ስትልክ እነርሱ ይፈጠራሉ የምድርንም ገጽ ታድሳለህ፡፡
31ለዘላለም ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ያህዌ በፍጥረቱ ደስ ይበለው፡፡
32ከላይ ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች ተራሮችን ሲዳስሳቸው ይጨሳሉ
33በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለያህዌ እዘምራለሁ በሕይወትም እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፡፡
34ደስታዬ በእርሱ ስለሆነ የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሰኘው፡፡
35ኅጥአን ከምድር ይጥፉ ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይኑሩ፡፡ ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።