1ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌ አመስግኚ የያህዌን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ፡፡
2ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመሰግኚ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፡፡
3ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር ይላል ደዌሽንም ሁሉ ይፈውሳል፡፡
4ሕይወትሽንም ከጥፋት ጉድጓድ ያድናል ምሕረትና ርኅራኄውን ያቀዳጅሻል፡፡
5ወጣትነትሽ እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ ሕይወትሽን በመልካም ነገር ያጠግባል፡፡
6ያህዌ ለተጨቆኑ ሁሉ፣ ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣል፡፡
7መንገዱን ለሙሴ፣ ሥራውንም ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ፡፡
8ያህዌ መሐሪና ይቅር ባይ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው፡፡
9እርሱ ሁልጊዜ አይገሥጽም ለዘላለምም አይቆጣም፡፡
10እንደ ኃጢአታችን አላደረግብንም እንደ በደላችንም አልከፈለንም፡፡
11ሰማይ ከምድር ከፍ የማለቱን ያህል እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ነው፡፡
12ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ በደልና ኃጢአታችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ፡፡
13አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ያህዌም ለሚፈሩት ይራራል፡፡
14እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና ትቢያ መሆናችንንም ይገነዘባል፡፡
15ሰው እኮ እንደ ሣር እንደሚያድግ የዱር አበባ ነው፡፡
16ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ድራሹ ይጠፋል፤ የነበረበት ስፍራ እንኳ አይታወቅም፡፡
17የያህዌ ምሕረት ግን ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፡፡ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጃቻቸው ዘመን በላያቸው ይሆናል፤
18ይህም ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ ትእዛዙንም በሚያከብሩት ላይ ይሆናል፡፡
19ያህዌ ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች፡፡
20እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክት ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኃያላን፣ ያህዌን አመስግኑ፡፡
21አገልጋዩ የሆናችሁ፣ ፈቃዱንም የምትፈጽሙ እናንተ የሰማይ ሰራዊት ያህዌን አመስግኑ፡፡
22በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ ያህዌን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ ያህዌን አመስግኚ፡፡