መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ምሳሌ 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጥበብ እየጮኸች አይደለምን? ማስተዋልስ ድምጿን ከፍ አላደረገችምን?
2ከመንገድ አጠገብ ባሉት ኮረብታዎች ጫፍ ላይ፣ መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ፣ ጥበብ ትቆማለች፡፡
3ወደ ከተማይቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በከተማይቱ መግቢያ አጠገብ፣ ትጣራለች፡፡
4እናተ ሰዎች፣ ወደ እናንተ እጣራለሁ፣ ድምጼንም ከፍ አድርጌ ወደ ሰው ልጆች እጮኸለሁ፡፡
5እናንተ ትምህርት ያላገኛችሁ፣ ጠንቃቃነትን ተማሩ፣ እናንተ እውቀትን የምትጠሉ፣ የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁ፡፡
6የከበሩ ነገሮችን እናገራለሁና አድምጡኝ፣ ከንፈሮቼ ሲከፈቱ ቀና የሆነውን ነገር እናገራለሁ
7አንደበቴ እውነትን ይናራልና፣ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጠላሉና፡፡
8ከአንደበቴ የሚወጡ ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ በእነርሱ ውስጥ ጠማማ ወይም አሳሳች ነገር የለውም፡፡
9ለሚያስተውል ሰው ቃሎቼ በሙሉ ቀና ናቸው፤ እውቀትን ለሚያገኙ ቃሎቼ ትክክለኛ ናቸው፡፡
10ከብር ይልቅ ተግሳጼን ምረጡ፣ ከንጹህ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ምረጡ፡፡
11እኔ ጥበብ፣ ከከበረ ዕንቁ እበልጣለሁና፤ ከምትመኙት ነገር በሙሉ ከእኔ ጋር የሚስተካከል የለም፡፡
12እኔ ጥበብ፣ ከጥንቃቄ ጋር እኖራለሁ፣ እውቀትና ነገሮችን ለይቶ ውሳኔ የመስጠት ኃይልም አለኝ፡፡
13እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢት፣ እብሪት፣ ክፉ መንገድና ጠማማ ንግግር እጠላለሁ፣ ፈጽሞም እጠላቸዋለሁ፡፡
14እኔ መልካም ምክርና እውነተኛ ጥበብ አለኝ፤ ማስተዋል አለኝ፣ ብርታትም የእኔ ነው፡፡
15ነገስታት፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትሃዊነት ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡
16መሳፍንቶች፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትህ ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡
17የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፣ ተግተው የሚፈልጉኝም ያገኙኛል፡፡
18ባለጠግነትና ክብር፣ ዘላቂነት ያለው ሃብትና ጽድቅም በእኔ ዘንድ አሉ፡፡
19ፍሬየ ከወርቅ ይበልጣል፣ ከነጠረ ወርቅም ይበልጣል፤ ስጦታየም ከንጹህ ብር ይበልጣል፡፡
20እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፣ ወደ ፍትህ በሚወስድ ጎዳና እጓዛለሁ፣
21ስለዚህ ለሚወዱኝ ሀብትን እሰጣቸዋለሁ፣ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ፡፡
22እግዚአብሄር ከመጀመርያ ፈጠረኝ፣ በቀድሞ ዘመን የስራው መጀመርያ ነኝ፡፡
23ከመጀመርያ፣ ምድር ከመፈጠሯ በፊት፣ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ተሾምሁ፡፡
24ውቅያኖሶች ሳይኖሩ፣ የውኃ ምንጮች ሳይፈልቁ በፊት፣ እኔ ተወልጄ ነበር፣
25ተራሮች ገና ሳይመሰረቱ፣ ከኮረብቶችም በፊት፣ እኔ ተወለድሁ፡፡
26እግዚአብሔር ምድርንና ሜዳዎቿን፣ የመጀመርያውን የዓለም አፈር እንኳ ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ፡፡
27እርሱ ሰማያትን ሲመሰርት፣ በውቅያኖስ ገጽ የአድማስን ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
28እርሱ በላይ ያሉትን ደመናት ባጸና ጊዜ፣ የውቅያኖስን ምንጮች በመሰረተ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
29ውሆች የእርሱን ትዕዛዝ አልፈው እንዳያጥለቀልቁ እርሱ ለባህር ድንበርን ባበጀለት ጊዜ፣ የምድርም መሰረት የት መሆን እንዳለበት በወሰነበት ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
30እኔ ዋና ሰራተኛ ሆኜ በአጠገቡ ነበርሁ፣ እኔ ዕለት በዕለት እርሱን ደስ አሰኘው ነበርሁ፣ ሁልጊዜ በፊቱ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
31የእርሱ በሆነው በመላው ዓለም ደስ ይለኝ ነበር፣ ደስታየም በሰው ልጅ ነበር፡፡
32አሁንም፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉና፡፡
33ምክሬን አድምጡ፣ ጥበበኞችም ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት፡፡
34እኔን የሚያደምጠኝ ደስተኛ ይሆናል፣ ዕለት በዕለት በመግቢያየ የሚተጋ፣ በቤቴም በሮች አጠገብ የሚጠብቀኝ፡፡
35እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፣ የእግዚአብሔርንም ሞገስ ያገኛል፡፡
36እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጎዳል፤ እኔን የሚጠሉኝ በሙሉ ሞትን ይወድዳሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።