1በበጋ ጊዜ እንደሚወርድ በረዶና በመከር ጊዜ እንደሚዘንብ ዝናብ፣ ክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም፡፡
2ድንቢጥ ከቦታ ቦታ እንደምትበርር፣ ጨረባም እንደምትሸመጥጥ፣ ያልተገባ እርግማን ማንም ላይ አይደርስም፡፡
3ጅራፍ ለፈረስ፣ ልጓምም ለአህያ እንደሆነ፣ በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው፡፡
4ለሞኝ መልስ አትስጠው፣ በሞኝነቱም አትተባበር፣ አለዚያ እንደ እርሱ ትሆናለህ፡፡
5ሞኝን እንደ ሞኝነቱ መልስለት፣ በሞኝነቱም ተባበረው፣ አለዚያ በዓይኖቹ ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል፡፡
6በሞኝ ሰው እጅ መልዕክትን የሚልክ ሁሉ የራሱን እግር ይቆርጣል ሁከትንም ይጠጣል፡፡
7የሰለሉ የሽባ እግሮች በሞኝ አፍ እንዳለ ምሳሌ ናቸው፡፡
8ለሞኝ ክብር መስጠት ድንጋይን በወንጭፍ እንደ ማሰር ነው፡፡
9በሰካራም እጅ ላይ ያለ እሾህ በሞኞች አፍ እንዳለ ምሳሌ ነው፡፡
10ሁሉንም ሰው የሚያቆስል ቀስተኛ፣ ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን እንደሚቀጥር ሰው ነው፡፡
11ውሻ ወደ ትውከቱ እንደሚመለስ፣ ሞኝነቱን የሚደጋግም ሞኝም እንዲሁ ነው፡፡
12በራሱ ዓይን ጥበበኛ እንደሆነ የሚያስብን ሰው አይተሃልን? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው፡፡
13ሰነፍ ሰው እንዲህ ይላል፣ “አንበሳ በመንገድ አለ! በውጭ በአውራ ጎዳና አንበሳ አለ፡፡”
14በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በአልጋው ላይ ይዟዟራል፡፡
15ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ሳህኑ ያስገባል፣ ነገር ግን እጁን ወደ አፉ ለመመለስ ጉልበት የለውም፡፡
16ሰነፍ ሰው ማስተዋል ካላቸው ከሰባት ሰዎች የበለጠ ጥበበኛ እንደሆነ በራሱ ዓይን ያስባል፡፡
17የውሻን ጆሮ እንደሚይዝ ሰው፣ የራሱ ባልሆነ ጥል ላይ የሚገባ መንገድ አላፊ ሰውም እንዲሁ ነው፡፡
18ተቀጣጣይ ቀስት እንደሚወራወር እብድ ሰው፣
19“የተናገርሁት እኮ ቀልዴን ነበር?” በማለት ጎረቤቱን የሚያታልል ሰው እንዲሁ ነው፡፡
20በእንጨት እጦት እሳት ይጠፋል፣ ሐሜት በሌለበትም ጥል ያቆማል፡፡
21ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ ጠበኛ ሰውም ሁከትን ያቀጣጥላል፡፡
22የሐሜት ቃላቶች እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፤ ወደ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችም ይወርዳሉ፡፡
23እንሚያቃጥሉ ከንፈሮችና እንደ ክፉ ልብ በብር ፈሳሽ የተለበጠ የሸክላ ድስት እንዲሁ ነው፡፡
24ሌሎችን የሚጠላ ሰው ስሜቱን በከንፈሮቹ ይሸነግላል፣ ተንኮሉን ግን በውስጡ ያኖራል፡፡
25ማራኪ የሆነ ንግግር ይናገራል፣ ነገር ግን አትመነው፣ በልቡ ውስጥ ሰባት ርኩሰቶች አሉና፡፡
26ምንም እንኳ ጥላቻው በሽንገላ የተሸፈነ ቢሆንም፣ ክፋቱ ግን በጉባኤ ይገለጣል፡፡
27ጉድጓድን የሚቆፍር ሰው እርሱ ይገባበታል፣ ድንጋይንም የሚያንከባልል ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል፡፡
28ውሸታም ምላስ የጎዳቸውን ሰዎች ይጠላል፣ ሸንጋይ አፍም ጥፋትን ያመጣል፡፡