መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ምሳሌ 23

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከገዢ ጋር ለመብላት ስትቀመጥ፣ በፊት ያለውን በጥንቃቄ አስተውል፣
2ከመጠን ያለፈ ምግብ መብላት የምትወድ ዓይነት ሰው ከሆንህ በጉሮሮህ ላይ ካራ አድርግ፡፡
3የእርሱ ጣፋጭ ምግቦች አያስጎምጁህ፣ በውሸት የመጣ ምግብ ነውና፡፡
4ባለጠጋ ትሆን ዘንድ ከመጠን በላይ አትልፋ፤ መቼ ማቆም እንዳለብህም ታውቅ ዘንድ ብልህ ሁን፡፡
5አይንህን በገንዘብ ላይ በጣልክ ጊዜ፣ እርሱ ይጠፋል፣ በድንገት ክንፍ ያወጣል እንደ ንስርም ወደ ሰማይ እየበረረ ይሄዳል፡፡፤
6የክፉ ሰውን፣ እጅግ በጣም ከርቀት በምግብህ ላይ በቅናት የሚመለከተውን ሰው ምግብ አትብላ፣ ጣፋጭ መብሎቹንም አትጎምጅ፣
7እርሱ የምግቡን ዋጋ የሚቆጥር ሰው ነውና፡፡ “ብላ፣ ጠጣ!” ይልሃል፣ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም፡፡
8ትንሽ የበላኸው ያስታውክሃል፣ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ፡፡
9ሞኝ ሰው ባለበት ንግግር አታድርግ፣ እርሱ የቃሎችህን ጥበብ ያንኳስሳልና፡፡
10የጥንቱን የድንበር የምልክት ድንጋይ አታንሳ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች እርሻ አትግፋ፣
11ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፣ እርሱ ጉዳያቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳል፡፡
12ልብህን ለተግሳጽ ጆሮህንም ለእውቀት ቃሎች ስጥ፡፡
13ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፣ በበትር ብትመታው አይሞትምና፡፡
14በበትር ብትመታው ነፍሱን ከሲኦል ታድናታለህ፡፡
15ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣ ያኔ ልቤ ደግሞ ደስተኛ ይሆናል፤
16ከንፈሮችህ ትክክለኛ የሆነውን በሚናገሩበት ጊዜ ውስጣዊ ሰውነቴ ሁሉ ደስ ይለዋል፡፡
17ልብህ በኃጢአተኞች እንዲቀና አትፍቀድ፣ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ተመላለስ፡፡
18ለወደፊት እርግጠኛ አለኝታ አለህ፣ ተስፋህም አይጠፋም፡፡
19ልጄ ሆይ፣ ስማኝ፣ ጥበበኛ ሁን ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ላይ አዘንብል፡፡
20ከሰካራሞች ወይም በሆዳምነት ስጋ ከሚበሉ ጋር አትተባበር፣
21ሰካራሞችና ሆዳሞች ድሃ ይሆናሉ፣ እንቅልፋምነትም ቁራጭ ጨርቅ ያስለብሳቸዋል፡፡
22የወለደህን አባትህን ስማ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት፡፡
23እውነትን የራስህ አድርጋት፣ አትሽጣትም፤ ጥበብን፣ ስርዓትንና ማስተዋልንም ገንዘብህ አድርግ፡፡
24የጻድቅ አባት በደስታ ይሞላል፣ ጥበበኛ ልጅንም የወለደ በልጁ ይደሰታል፡፡
25አባትህና እናትህን ደስ አሰኛቸው፣ የወለደችህ እናትህም ሐሴት ታድርግ፡፡
26ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፣ አይኖችህም የእኔን መንገድ ያስተውሉ፡፡
27ዝሙት አዳሪ ሴት ጥልቅ ጉድጓድ፣ የሌላ ሰውም ሚስት ጠባብ ጉድጓድ ናትና፡፡
28እንደ ሌባ አድፍጣ ጥጠብቃለች፣ በሰዎችም መካከል የከዳተኞችን ቁጥር ታበዛለች፡፡
29ዋይታ የማን ነው? ሃዘን የማን ነው? ጠብስ የማን ነው? ማጉረምረም የማን ነው? ያለ ምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን መቅላት የማን ነው?
30ወይን ጠጅ በመጠጣት የሚቆዩ፣ ድብልቅ ወይን ጠጅ የሚቀምሱ ሰዎች ነው፡፡
31በቀላ ጊዜ ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት፣ በብርጭቆ ውስጥ መልኩ ባንጸባረቀ ጊዜ የሚያንጸባርቅ በሆነ ጊዜ፣ ስትጠጣውም ያለ ምንም ችግር በገባ ጊዜ፡፡
32በመጨረሻ እንደ እባብ ይናከሳል፣ እንደ እፉኝትም ይናደፋል፡፡
33አይኖችህ አዲስ ነገሮችን ያያሉ፣ ልብህም ጠማማ ነገሮችን ይናገራል፡፡
34በባህር ከፍታ ላይ እንደተኛ፣ በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ፡፡
35“መቱኝ!” “ነገር ግን አልተጎዳሁም፡፡ ደበደቡኝ፣ ነገር ግን አልተሰማኝም፡፡ መቼ ይሆን የምነቃው? ሌላ መጠጥ እፈልጋለሁ፡፡” ትላለህ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።