መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ምሳሌ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ብትቀበልና ትእዛዛቴን በአንተ ዘንድ ብታኖር፣
2ጥበብን ብታደምጥና ልብህን ወደ እውቀት ብትመልስ፡፡
3እውቀትን ለማግኘት ብትጣራና ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለማስተዋል ብትጮህ፣
4ብርን አጥብቀህ እንደምትፈልግ እርስዋንም ብትፈልጋት፣ የተሰወረ ሃብትን እንደምትፈልግ እንደዚሁ ማስተዋልን ብትሻት፣
5በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ፡፡
6እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፣ እውቀትና ማስተዋል ከአንደበቱ ይወጣሉ፡፡
7እርሱ ደስ ለሚያሰኙት ጥልቅ ጥበብን ያከማቻል፣ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱ ጋሻ ነው፣
8የፍትህን መንገድ ይጠብቃል፣ ለእርሱ ታማኞች ለሆኑት ደግሞ መንገዳቸውን ያጸናል፡፡
9በዚያን ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትህንና ሚዛናዊነትን እንደዚሁም ማንኛውንም መልካም መንገድ ትገነዘባለህ፡፡
10ጥበብ ወደ ልብህ ትመጣለችና፣ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፡፡
11የመለየት ችሎታ ይጠብቅሃል፣ ማስተዋል ይጋርድሃል፡፡
12እነዚህ ከክፋት መንገድ፣ ጠማማ ንግግር ከሚናገሩ ሰዎች፣
13ትክክለኛውን መንገድ ከተዉና በጨለማ መንገድ ከሚሄዱ ይጠብቁሃል፡፡
14እነዚህ ክፋትን ሲያደርጉ ደስ ይላቸዋል፣ በጠማማነት ሃሴት ያደርጋሉ፡፡
15ጠማማ መንገድን ይከተላሉ፣ አካሄዳቸውን ደግሞ በአታላይነታቸው ይደብቃሉ፡፡
16ጥበብና ልባምነት ከአመንዝራ፣ ከጀብደኛና በንግግሯ ከምታታልል ሴት ያድኑሃል፡፡
17ይህች ሴት የወጣትነት በልዋን የተወችና የአምላክዋን ቃል ኪዳን የረሳች ናት፡፡
18ቤቷ ወደ ሞት ያዘነበለ ስለሆነ አካሄዷ በመቃብር ወዳሉት ሙታን ይመራሃል፡፡
19ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ እንደገና አይመለሱም፣ የሕይወትንም መንገድ አያገኙም፡፡
20ስለዚህ አንተም በመልካም ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ፣ የጻድቃንን መንገድ ትከተላለህ፡፡
21ጻድቃን ቤታቸውን በምድሪቱ ይሰራሉና፣ እነዚህ ነቀፋ የሌለባቸው ደግሞ በእርሷ ጸንተው ይኖራሉና፡፡
22ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይቆረጣሉ፣ ታማኝነት የሌላቸውም ከእርሷ ይወገዳሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።