መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ምሳሌ 18

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ራሱን ከሰው የሚለይ የራሱን ምኞት ይፈልጋል፣ ትክክለኛውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል፡፡
2ሞኝ ሰው በማስተዋል ደስታን አያገኝም፣ በራሱ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር በመግለጥ እንጂ፡፡
3ክፉ ሰው ሲመጣ፣ ንቀት ከእፍረትና ከስድብ ጋር አብረውት ይመጣሉ፡፡
4ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሃ ናቸው፤ የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው፡፡
5ለክፉው ማድላት፣ ጽድቅን ለሚያደርጉም ፍትህን ማጉደል መልካም አይደለም፡፡
6የሞኝ ከንፈሮች ጥልን ያመጡበታል፣ አፉም በትርን ትጠራለች፡፡
7የሞኝ አፍ መጥፊያው ነው፣ በከንፈሮቹም ራሱን ወጥመድ ውስጥ ይጥላል፡፡
8የሐሜት ቃላት እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፣ ወደ ሰውነት ውስጣዊ ክፍሎች ጠልቀው ይገባሉ፡፡
9በስራው ችላ የሚልም ብዙውን የአጥፊ ሰው ወንድም ነው፡፡
10የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ይድናል፡፡
11የባለጸጋ ሐብት የእርሱ የተመሸገ ከተማ ነው፣ ሃሳቡም እንደ ረዥም ግንብ ነው፡፡
12ከውድቀቱ በፊት የሰው ልብ ትዕቢተኛ ይሆናል፣ ትህትና ግን ክብርን ቀድሞ ይመጣል፡፡
13ከማድመጡ በፊት የሚመልስ ሰው ሞኝነትና ዕፍረት ይሆንበታል፡፡
14የሰው መንፈስ ሕመምን ትታገሳለች፣ የተሰበረን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?
15የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፣ የጠቢብም ጆሮ ይፈልገዋል፡፡
16የሰው ስጦታ መንገዱን ትከፍትለታለች በተከበሩም ሰዎች ፊት ታቆመዋለች፡፡
17ወደ ፍርድ ቀድሞ በመምጣት ጉዳዩን የሚያሰማ ጻድቅ ይመስላል፣ ይህ ግን የሚሆነው ተቀናቃኙ መጥቶ እስከሚጠይቀው ድረስ ነው፡፡
18እጣ ማውጣት ክርክርን ያቆማል፣ ሃይለኛ ጠላቶችንም ትለያለች፡፡
19የተበደለ ወንድምን መርታት ጠንካራ ከተማን ከማሸነፍ ይልቅ በጣም የከበደ ነው፣ ጠብም እንደ ግንብ ብረት ነው፡፡
20የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፤ በንፈሮቹም ምርት ይረካል፡፡
21ሞትና ሕይወት በምላስ ላይ ናቸው፣ የሚወዱትም ፍሬዋን ይበላሉ፡፡
22ሚስትን ያገኘ መልካምን ነገር አግኝቷል፣ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን አግኝቷል፡፡
23ድሃ ሰው ምህረትን ይለምናል፣ ሃብታም ግን በማመናጨቅ ይመልሳል፡፡
24ብዙ ጓደኞች ያለው ሰው በእነርሱ አማካኝነት ወደ ጥፋት ይመጣል፣ ከወንድም የቀረበ ጓደኛ ግን አለ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።