መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ምሳሌ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል፣ በትክክለኛ ሚዝን ግን ሚዛን ደስ ይለዋል፡፡
2ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፣ ከትህትና ጋር ግን ጥበብ ትመጣለች፡፡
3የቅኖች ሀቀኝነታቸው ይመራቸዋል፣ የከዳተኞች ጠማማ መንገድ ግን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል፡፡
4በቁጣ ቀን ሀብት ዋጋ ቢስ ነው፣ ጽድቅ ግን ከሞት ታድንሃለች፡፡
5ነቀፋ የሌለበት ሰው ጽድቅ መንገዱን ያቀናለተል፣ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይወድቃሉ፡፡
6እግዚብሔርን ደስ የሚያሰኙ ሰዎች ጽድቃቸው ትታደጋቸዋለች፣ ከዳተኞች ግን በክፉ ምኞታቸው ይጠመዳሉ፡፡
7ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ይጠፋል፣ በብርታቱ የተመካበት ተስፋም ከንቱ ይሆናል፡፡
8ጽድቅን የሚያደርግ ከመከራ ይድናል፣ ይልቁንም መከራው በክፉው ይመጣበታል፡፡
9አምላክ የለሽ ሰው በአንደበቱ ጎረቤቱን ያጠፋል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን በእወቀት ይድናሉ፡፡
10ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበለጽጉ ከተማ ትደሰታለች፤ ክፉዎች ሲጠፉ የደስታ ጩኸት ይሆናል፡፡
11እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኙ ሰዎች መልካም ስጦታ ከተማ ታላቅ ትሆናለች፤ በክፉዎች አንደበት ግን ከተማ ትፈርሳለች፡፡
12ጓደኛውን የሚንቅ ሰው አእምሮ የጎደለው ነው፣ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል፡፡
13ለሐሜት የሚሄድ ሰው ምስጢርን ይገልጣል፣ ታማኝ ሰው ግን ምስጢርን ይሰውራል፡፡
14በጥበብ አልባ አመራር ሕዝብ ይወድቃል፣ የመካሮች ብዛት ባለበት ግን ድል ይመጣል፡፡
15ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራን ይቀበላል፣ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ዋስ ለመሆን የሚጠላ ሰው ግን ይድናል፡፡
16ሞገስ ያላት ሴት ክብር ታገኛለች፣ ጨካኝ ሰዎች ግን ሀብትን ብቻ ያገኛሉ፡፡
17ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፣ ጨካኝ ሰው ግን ራሱን ይጎዳል፡፡
18ክፉ ሰው ደመወዙን ለማግኘት ይዋሻል፣ ጽድቅን የሚዘራ ግን የእውነትን ደመወዝ ይሰበስባል፡፡
19ጽድቅን የሚያደርግ ታማኝ ሰው በሕይወት ይኖራል፣ ክፋትን የሚያደርግ ግን ይሞታል፡፡
20እግዚአብሔር ጠማማ ልብ ያላቸውን ይጠላል፣ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል፡፡
21ክፉ ሰዎች ሳይቀጡ እንደማይቀሩ ይህን እርግጠኛ ሁን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ዘሮች ግን ይድናሉ፡፡
22በአሳማ አፍንጫ እንደተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ ማስተዋል የሌላትም ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት፡፡
23ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ምኞት መልካም ውጤት ያመጣል፣ ክፉ ሰዎች ግን ተስፋ ሊያደርጉት የሚችሉት መቅሰፍት ብቻ ነው፡፡
24ዘርን የሚዘራ አንድ ሰው አለ፣ እርሱ ይበልጥ ይሰበስባል፤ ሌላ ደግሞ የማይዘራ አለ፣ እርሱ ይደኸያል፡፡
25ለጋስ ሰው ይበለጽጋል፣ ለሌሎች ውኃ የሚሰጥ ደግሞ ለራሱም ውኃ ያገኛል፡፡
26እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው ሕዝብ ይረግመዋል፣ በሚሸጠው ግን መልካም ስጦታዎችን በራሱ ላይ እንደ አክሊል ይጎናጸፋል፡፡
27መልካምን ነገር ተግቶ የሚፈልግ ሞገስን ይፈልጋል፣ ክፉን የሚፈልግ ግን ክፉ በራሱ ላይ ይመጣበታል፡፡
28በባለጠግነታቸው ላይ የሚታመኑ ሰዎች ይወድቃሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፡፡
29በቤተሰቡ ላይ ሁከትን የሚያመጣ ሰው ነፋስን ይወርሳል፣ ሞኝም ሰው በልቡ ጥበበኛ ለሆነው ሰው አገልጋይ ይሆናል፡፡
30ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች እንደ ሕይወት ዛፍ ይሆናሉ፣ ሁከት ግን ሕይወትን ያጠፋል፡፡
31ጽድቅን የሚደርጉ ሰዎች ለሰሩት ስራ የሚገባቸውን የሚቀበሉ ከሆነ፣ ይልቁንስ ክፉዎችና ኃጢአተኞች እንዴት አይቀበሉ!
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።