1የሰሎሞን ምሳሌዎች፡፡ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሃዘንን ያመጣል፡፡
2በክፋት የተከማቸ ሃብት ምንም ጥቅም የለውም፣ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል፡፡
3እግዚአብሔር በጽድቅ የሚሄዱትን እንዲራቡ አያደርግም፣ የክፉዎችን ምኞት ግን ያከሽፋል፡፡
4የሰነፍ እጅ ድሃ ታደርጋለች፣ የትጉ እጅ ግን ብልጽግናን ታመጣለች፡፡
5ጥበበኛ ልጅ በበጋ ምርትን ይሰበስባል፣ በመከር መተኛት ግን ለእርሱ ውርደት ነው፡፡
6የእግዚአብሔር ስጦታ በጻድቃን ራስ ላይ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል፡፡
7ጻድቅ ሰው ስለ እርሱ ስናስብ ደስ እንድንሰኝ ያደርገናል፣ የክፉ ሰው ስም ግን ይጠፋል፡፡
8አዋቂዎች ትእዛዛትን ይቀበላሉ፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ጥፋት ይሄዳል፡፡
9በሀቀኝነት የሚሄድ ሰው ተማምኖ ይሄዳል፣ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይጋለጣል፡፡
10በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ይጠፋል፡፡
11ጽድቅን የሚያደርግ ሰው አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋትን ይደብቃል፡፡
12ጥላቻ ጠብን ያነሳሳል፣ ፍቅር ግን ስህተትን ሁሉ ይሸፍናል፡፡
13በአስተዋይ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፣ በትር ግን አእምሮ ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው፡፡
14ጥበበኛ ሰዎች እውቀትን ይሰበስባሉ፣ የሞኝ አፍ ግን ጥፋትን ያመጣል፡፡
15የባለጠጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤ የድሆች ድህነት ግን መጥፊያቸው ነው፡፡
16የጻድቅ ሰው ደመወዝ ወደ ሕይወት ይመራል፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ወደ ኃጢአት ይመራቸዋል፡፡
17እርምትን ለሚከተል ሰው ወደ ሕይወት የምትመራ ጎዳና አለች፣ ተግሳጽን የማይቀበል ሰው ግን ይስታል፡፡
18ጥላቻን የሚደብቅ ሰው ሐሰተኛ ከንፈሮች አሉት፣ ሐሜትን የሚያስፋፋ ሞኝ ነው፡፡
19በብዙ ቃላቶች ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፣ ለሚናገረው ነገር ጥንቃቄ የሚደርግ ሰው ግን ጥበበኛ ነው፡፡
20የጻድቅ ሰው ምላስ የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ዋጋ የለውም፡፡
21የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ያንጻሉ፣ ሞኞች ግን ባለማማዛዘናቸው ምክንያት ይሞታሉ፡፡
22የእግዚአብሔር መልካም ስጦታዎች ሃብትን ያመጣሉ፣ መከራንም አያክልበትም፡፡
23ክፋት የሞኞች ጨዋታ ነው፣ ጥበብ ግን ለአስተዋይ ሰው ደስታ ነው፡፡
24የክፉ ሰው ፍርሃት ድንገት ይደርስበታል፣ የጻድቅ ሰው ምኞት ግን ይፈጸማል፡፡
25ክፉ ሰዎች እንደሚያልፍ አውሎ ነፋስ ናቸው፣ ከዚያም በኋላ አይገኙም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን ለዘላለም የሚኖሩ መሰረት ናቸው፡፡
26በጥርስ ላይ ያለ ሆምጣጤ፣ በዓይንም ውስጥ ያለ ጢስ እንደሚጎዳ፣ ሰነፍ ሰው ለሚልኩት እንዲሁ ነው፡፡
27እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡
28ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ተስፋ ደስታቸው ነው፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡
29የእግዚአብሔር መንገድ ሃቀኞችን ይጠብቃቸዋል፣ ለክፉዎች ግን መጥፊያቸው ነው፡፡
30ጽድቅን የሚያደርጉ ፈጽሞ አይወድቁም፣ ክፉዎች ግን በምድሪቱ አይቀሩም፡፡
31ከጻድቃን አፍ የጥበብ ፍሬ ይወጣል፣ ጠማማ ምላስ ግን ይቆረጣል፡፡
32የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢ የሆነውን ነገር ያውቃሉ፣ የክፉዎች አፍ ግን የሚያውቀው ጠማማ የሆነውን ነገር ብቻ ነው፡፡