1በክርስቶስ መበረታታት ካላችሁ፤ከፍቅሩም መጽናናት ካላችሁ፤የመንፈስም ኅብረት ካላችሁ፤እርስ በእርሳችሁም ደግነትና ርኅራኄ ካላችሁ።
2ስለዚህ በአንድ አሳብ፤ በፍቅር፤ በመንፈስ አንድነት፤በአንድ ዓላማ እየተስማማችሁ ደስታዬ እንዲፈጸም አድርጉት።
3በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ።
4እንዲሁም እያንዳንዳእሁ የራሳችሁን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም አስቡ።
5በኢየሱስ ክርስቶስ የነበረ አሳብ በእናንተም ደግሞ ይኑር፤
6እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ።
7የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ።
8እንዲሁም እስከ ሞት፤ያውም እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
9ስለዚህም እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ሰጠው።
10በዚህም ምክንያት ጉልበት ሁሉ በሰማይና በምድር፤ ከምድርም በታች ሁሉ በኢየሱስ እግሮች በታች እንዲንበረከኩ ነው።
11አንደበትም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ብሎ እንዲመሰክር ነው።
12ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ እኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ እንደምትታዘዙ፥ይልቁንም አሁን ከእናንተ በራቅሁበት ጊዜ ይበልጥ ታዛዦች እንድትሆኑ ነው።
13በፍርሃትና በመንቀጥቅቀጥም መዳናችሁን ሥሩ። ምክንያቱም ለመልካምነቱ መፍቃዱንና ማድረግን በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነው።
14ማናቸውንም ነገር ሳታጉረምግሙና ሳትከራከሩ አድርጉ።
15ይህን በማድረግ ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ታማኝ የአግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ። በዚህ በጠማናና በመጥፎ ትውልድ መካከል በዚህ ዓለም እንደ ደማቅ ብርሃን ታበራላችሁ።
16ሕይወት የሚገኝበትን ቃል አጥብቃችሁ በምትይዙበት ጊዜ በከንቱ እንዳልሮጥሁና በከንቱም እንዳልደከምሁ ክርስቶስ በሚመለስበት ቀን ለማክበር ምክንያት ሊኖረኝ ይችላል።
17ነገር ግን ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት እንደ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል። ከሁላችሁ ጋር ታላቅ ደስታ እደሰታለሁ።
18እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ እናንተም ከእኔ ጋር ደስተኞች ትሆናላችሁ።
19ነገር ግን እናንተ እንዴት እየሠራችሁ እንዳላችሁ ሰምቼ እንድጽናና ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ ፈጥኜ እንደምልክ በጌታ በኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።
20ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቲዎስ በስተቀር ሌላ ሰው የለኝም።
21ሌሎቹ ግን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ስለሚፈልጉ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ግድ የላቸውም።
22ነገር ግን ጢሞቲዎስ ልጅ አባቱን እንደሚያገለግል ከእኔ ጋር ወንጌልን በማሠራጨት እንዳገለገለና ስለታማኝነቱም የተመሰከረለት መሆኑን እናንተም ታውቃላችሁ።
23ስለዚህ የእኔን ሁኔታ እንዳወቅሁ በፍጥነት ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ እንደምልክላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
24እንዲያውም እኔ ራሴ በቶሎ ወደ እናንተ እንደምመምጣት በጌታ እተማመናለሁ።
25ነገር ግን ኤጳፍሮዲቱስን መልሼ ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እርሱ እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜና ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ባልደረባዬ ነው።
26እርሱን ወደ እናንተ የምልከውም ሁላችሁንም ለማየት በመናፈቁና እናንተም መታመሙን በመስማታችሁ ስለ ተጨነቀ ነው። በእርግጥ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት አደረገለት።
27ከሕመሙ መዳኑ ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ሐዘን በሐዘን ላይ እንዳይደረርብኝ ለእኔም ጭምር ነው።
28ስለዚህ እናንተ እርሱን በማየት እንድትደሰቱና የእኔም ሐዘን እንዲቃለል እርሱን ወደ እናንተ ለመላክ ከፍተኛ ፍላጎት አድሮብኛል።
29እንግዲህ ኤጳፍሮዲቱስን በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት። እንደ እርሱ ያሉትን ሰዎች አክብሩአቸው ።
30በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን በእናንተ ቦታ ሆኖ ሲያገለግለኝና የሚያስፈልገኝን ለማሟላት ስለ ክርስቶስ ሥራ በማለት ለሕይወቱ ሳይሳሳ በማድረግ ለሞት ተቃርቦ ነበር።