መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ፊልጵስዩስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቲዎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ በፊልጵስዩስ ከተማ ከእረኞችና ከዲያቆናት ጋር ለሚኖሩ ሁሉ።
2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ስላም ለአናንተ ይሁን።
3ስለእናንተ በማስብበት ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
4ስለ ሁላችሁም በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ በደስታ እጸልያለሁ።
5ከመጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ወንጌል በሚሰበክበት ሥራ ስላሳያችሁት ትብብራችሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
6ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።
7እናንተ በልቤ ስላላችሁ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰብ ይኖርብኛል። በእስራቴና ስለ ወንጌል በመቆሜ ስለእርሱም በመመስከሬ ሁላችሁም በጸጋ ተባባሪዎች ሆናችኋል።
8በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር ሁላችሁንም እንድምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
9ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ።
10ይህን የምጸልይበት ምክንያት የተሻለውን ነገሮችን መርምራችሁ እንድታውቁ እንዲሁም ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ቀን ንጹኃንና ነውር የሌለባችሁ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።
11ይህ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ ተሞልታችሁ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና እንዲሆን ነው።
12ወንድሞች ሆይ፥በእኔ ላይ የደረሰው ሁሉ ወንጌል በጣም እንዲስፋፋ እንዳደረገ እንድታውቁ እወዳለሁ።
13እኔም የታሰሁት በክርስቶስ ምክንያት መሆኑን የቤተ መንግሥት ጠበቂዎችና ሌሎችም እዚያ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ ሆኖአል።
14በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ወንድሞች ከሆኑት ብዙዎቹ የበለጠ ከቀድሞ ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሃት ለመናገር ድፍረት አግኝተዋል።
15በርግጥ አንዳንዶቹ የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩት በቅናትና በፉክክር መንፈስ ነው፤ሌሎቹ ግን ክርስቶስን የሚሰብኩት በቅን ልቡና ነው።
16እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል በቅን ልቡና የሚሰብኩት ከፍቅር የተነሳ ነው፤እነርሱም እኔ ስለወንጌል ቆሜ በመከራከርይ መታሰሬን ያውቃሉ።
17እነዚያ ግን ስለ ክርስቶስ የሚሰብኩት በራስ ወዳድነትና ቅንነት በሌለበት አስተሳሰብ ነው። በእስራቴም ላይ ተጨማሪ መከራ ሊያመጡብኝ አስበው ነው።
18ታዲያ ምን ይደረግ? በርግጥ በዚህ ደስ ይለኛል፤በማስመሰል ወይም በእውነት በሁሉም መንገድ ክርስቶስ ይሰበካል።
19ምክንያቱም በእናንተ ጸሎትና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ርዳታ ነጻ እንደምወጣ አውቃለሁ።
20እንደማላፍርበት በሙሉ መተማመ እጠባበቃለሁ። ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና በተለይም ዛሬም በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።
21ስለዚህ ለእኔ ሕይወት ማለት በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት ማትፍረፍ ነው።
22ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።
23ምክንያቱም በእነዚህ በሁለቱ አሳቦች መካከል ተወጥሬአለሁ። በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ።
24ሆኖም በሥጋ መኖሬ ለእናንተ የበለጠ አስፈላጊ ነው።
25እምነታችሁ እንዲያድግና ደስታን እንድታገኙ እንደምቆይና ከሁላችሁም ጋር እንደምቀጥል ስለዚህ ነገር እተማመናሉ።
26በዚህ ምክንያት እኔም እንደገና ወደ እናንተ ስመጣት ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ በእኔ ትመካላችሁ።
27እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁ ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ለወንጌልም እምነት በኅብረት መጋደላችሁን እሰማ ዘንድ ነው።
28ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን፤ ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳናችሁ ምልክት ነው።
29ምክንያቱም ከክርስቶስ የተነሳ ይህ የተሰጣችሁ አገልግሎት በእርሱ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ምክንያት መከራ እንድትቅበሉም ጭምር ነው።
30ስለዚህ አሁን ከእኔ ጋር የመከራ ተካፋዮች ሆናችኋል፤ ይህም መከራ ከዚህ በፊት ደርሶብኝ ያያችሁትና አሁንም እየደረሰብኝ መሆኑን የሰማችሁት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።