መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“አሮንን እንዲህ በለው፣ ‘ሰባቱ መብራቶች በምትለኩሳቸው ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን ይስጡ፡፡’”
3አሮን ይህን አደረገ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን እንዲሰጡ መብራቶቹን በመቅረዙ ላይ ለኮሳቸው፡፡
4መቅረዙ የተሰራው በዚህ መንገድ ነበር፡፡ ያህዌ አሰራሩን ለሙሴ አሳይቶት ነበር፡፡ ከመሰረቱ እስከ ጫፍ በአበባ መልክ የዋንጫ መልክ ቅርጽ አስይዘህ ወርቁን ቀጥቅጠህ አብጀው፡፡
5እንደገና፣ ያህዌ ሙሴን እንዲሀ ሲል ተናገረው፣
6“ከእስራኤል ሰዎች መሃል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው፡፡
7እነርሱን ለማንጻት ይህን አድርግ፣ የማንጻት ውሃ እርጫቸው፡፡ ፀጉራቸው በሙሉ እንዲላጩ፣ ልብሶቻቸውን እንዲያጥቡ፣ እና በዚህ መንገድ ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፡፡
8ከዚያ ጥጃና በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት የእህል ቁርባን ይውሰዱ፡፡ ሌላ ጥጃ ለኃጢአት መስዋዕት ያዘጋጁ፡፡
9ሌዋውያኑን ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አቅርባቸውና መላውን የእስራኤል ማህበረሰብ ሰብስብ፡፡
10በእኔ በያህዌ ፊት ሌዋውያንን አቅርብ፡፡ የእስራኤል ሰዎች እጃቸውን በሌዋውያን ላይ ይጫኑ፡፡
11አሮን ሌዋውያኑን በእኔ ፊት ያቅርባቸው፣ የእስራኤልን ህዝብ ወክለው በእርሱ ፊት ከፍ አድርገው እንደሚያቀርቡ አቅርባቸው፡፡ ሌዋውያን እኔን እንደሚያገለግሉ እርሱ ይህን ያድርግ፡፡
12ሌዋውያኑ በበሬዎቹ ላይ እጃቸውን ይጫኑ፡፡ ሌዋውያኑን ለማስተሰርይ፣ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ኮርማ አቅርቡ፣ ደግሞም ሌላውን ኮርማ የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ ለእኔ አቅርብ፡፡
13ሌዋውያኑን በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፣ እናም እንደ ሚወዘወዝ መሥዋዕት ለእኔ ከፍ አድርገህ አቅርባቸው፡፡
14በዚህ መንገድ ሌዋውያኑን ከእስራኤል ሰዎች መሃል ለያቸው፡፡ ሌዋውያን ለእኔ ይለዩ፡፡
15ከዚያ በኋላ ሌዋውያኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ለአገልግሎት ይግቡ፡፡ እነርሱን አንጻቸው፡፡ እንደ ስጦታ ለእኔ ከፍ አድርገህ አንሳቸው፡፡
16ከእስራኤል ህዝብ መሀል እነርሱ ሙሉ ለሙሉ የእኔ ናቸውና ይህን አድርግ፡፡ ከእስራኤል ወገን በኩር ሁሉ፣ ማህጸን ከከፈተው ከእያንዳንዱ ወንድ ልጅ ቦታውን ይወስዳሉ፡፡ እኔ ሌዋውያንን ለራሴ ለይቻለሁ፡፡
17ከሰውም ሆነ ከእንስሳው የእስራኤል ህዝብ በኩሩ ሁሉ የእኔ ነው፡፡ በግብፅ ምድር የበኩሩን ህይወት ሁሉ በወሰድኩ ቀን፣ እኔ እናንተን ለራሴ ለየኋችሁ፡፡
18በበኩሩ ሁሉ ምትክ፣ ከእስራኤል ሰዎች መሀል ሌዋውያንን ወሰድኩ፡፡
19ሌዋውያንን ለአሮንና ለልጆቹ እንደ ስጦታ ሰጠኋቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የእስራኤልን ሰዎች ሥራ ይስሩ ዘንድ ከእስራኤል ሰዎች መሃል ወሰድኳቸው፡፡ ወደተቀደሰው ስፍራ ሲቀርብ ምንም ጥፋት እንዳይደርስባቸው ለእስራኤል ሰዎች እንዲያስተሰርዩ እነርሱን ሰጠኋቸው፡፡”
20ሙሴ፣ አሮንና መላው የእስራኤል ህዝብ ይህንን ከሌዋውያን ጋር አደረጉ፡፡ ሌዋውያንን በሚመለከት ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ የእስራኤል ሰዎች ከእነርሱ ጋር ይህን አደረጉ፡፡
21ሌዋውያን ልብሶቻቸውን በማጠብ ራሳቸውን ከኃጢአት አነጹ፡፡ አሮን ለያህዌ ስጦታ አድርጎ አቀረባቸው፤ ደግም ይነጹ ዘንድ የንስሃ ማስተስረያ አደረገላቸው፡፡
22ከዚያ በኋላ፣ ሌዋውያኑ በአሮንና በአሮን ልጆች ፊት አገልግሎታቸውን ይሰጡ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፡፡ ይህም ያህዌ ስለ ሌዋውያን ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡ ሌዋውያንን በሙሉ በዚህ መንገድ ተቀበሉ፡፡
23ያህዌ እንደገና ለሙሴ ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፣
24“ይህ ሁሉ፤ ሃያ አምስት አመት እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ላላቸው ሌዋውያን ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል መምጣት አለባቸው፡፡
25አምሳ አመት ሲሞላቸው በዚህ መንገድ ማገልገላቸውን ያቁሙ፡፡ በዚያ ዕድሜ መደበኛ አገልግሎታቸውን ያቁሙ፡፡
26በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ወንድሞቻቸውን ሊያግዙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዕድሜያቸው አምሳ ከሆነ በኋላ በዚህ መንገድ አያገለግሉ፡፡ ለሌዋውያን በእነዚህ ጉዳዮች ሁሉ መመሪያ ልትሰጣቸው ይገባል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።