መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ማደሪያ ድንኳኑን በጨረሰ ቀን፣ ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር ቀብቶ ለያህዌ ለየው፡፡ በመሰዊያውና በዕቃዎቹ ላይ እንዲሁ አደረገ፡፡ ቀብቶ ለያህዌ ለያቸው፡፡
2በዚያ ቀን፣ የእስራኤል መሪዎች፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች አባቶች መስዋዕቶችን አቀረቡ፡፡ ጎሳዎቹን የሚመሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የህዝብ ቀጠራውን ተቆጣጠሩ፡፡
3መስዋዕቶቻቸውን ያህዌ ፊት አመጡ፡፡ ስድስት የተሸፈኑ ሰረገሎችና አስራ ሁለት በሬዎች አመጡ፡፡ ለየሁለቱ መሪዎች አንድ ሰረገላ አመጡ፣ እያንዳንዱ መሪ አንድ በሬ አመጣ፡፡ እነርሱ እነዚህን ነገሮች በማደሪያው ድንኳን ፊት አቀረቡ፡፡
4ከዚያም ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣
5“መስዋዕታቸውን ከእነርሱ ተቀበልና ለመገናኛው ድንኳን ሥራ አውላቸው፡፡ ለሥራው እንደሚያስፈልጋቸው ለእያንዳንዱ፣ መስዋዕቶቹን ለሌዋውያን ስጥ፡፡”
6ሙሴ ሰረገሎቹንና በሬዎቹን ወስዶ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው፡፡
7ለጌድሶናውያን ተውልዶች ለስራቸው እንደሚያስፈልግ ሁለት ሰረገላዎችና አራት በሬዎች ሰጠ፡፡
8ለሜራሪ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር በኩል አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጠ፡፡ ይህን ያደረገው ሥራቸው ይህን ስለሚጠይቅ ነው፡፡
9ለቀዓት ትውዶች ከእነዚህ ነገሮች ምንም አልሰጠም፣ ምክንያቱም የእነርሱ የሥራ ድርሻ የያህዌ የሆኑትን ነገሮች በገዛ ትከሻቸው ከመሸከም ጋር የተያያዘ ነው፡፡
10መሪዎቹ ሙሴ መሰዊያውን በቀባ ዕለት ስጦታዎቻቸውን ለመሰዊያው መቀደስ ሰጡ፡፡ መሪዎቹ መስዋዕቶቻቸውን በመሰዊያው ፊት አቀረቡ፡፡
11ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እያንዳንዱ መሪ ለመሰዊያው መቀደስ በራሱ ቀን መስዋዕቱን ማቅረብ አለበት፡፡”
12በመጀመሪያው ቀን፣ ከይሁዳ ጎሳ የሆነው፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፣ መስዋዕቱነ አቀረበ፡፡
13መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የብር ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሳህን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሁለትም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
14በተጨማሪም በእጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሃን ሰጠ፡፡
15ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በግ ሰጠ፡፡
16ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
17ሁለት በሬዎች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መስዋዕት ነበር፡፡
18በሁለተኛው ቀን፣ የይሳኮር መሪ፣ የሶገር ልጅ ናትናኤል፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
19አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
20በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
21ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
22ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
23ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሶገር ልጅ የናትናኤል መስዋዕት ነበር፡፡
24በሶስተኛው ቀን የዛብሎን መሪ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
25አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
26በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
27ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
28ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
29ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኬሎን ልጅ የኤልያብ መስዋዕት ነበር፡፡
30በአራተኛው ቀን፣ የሮቤል ትውልድ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
31መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
32በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
33ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
34ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
35ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሰዲዮር ልጅ የአሌሊሱር መስዋዕት ነበር፡፡
36በአምስተኛው ቀን፣ የስምዖን ትውልድ መሪ፣ የሱሪሰዳይ ልጅ ስልሚኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
37መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
38በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ።
39ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
40ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
41ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሱሪሰዳይ ልጅ የስልሚኤል መስዋዕት ነበር፡፡
42በስድስተኛው ቀን፣ የጋድ ትውልድ መሪ፣ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
43መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
44በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
45ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
46ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
47ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡
48በሰባተኛው ቀን፣ የኤፍሬም ትውልድ መሪ፣ የዓመሁድ ልጅ ኤሊሳማ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
49መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
50በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
51ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
52ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
53ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡
54በስምንተኛው ቀን፣ የምናሴ ትውልድ መሪ፣ የፍደሱር ልጅ ገሚልኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
55መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
56በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
57ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
58ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
59ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡
60በዘጠነኛው ቀን፣ የብንያም ትውልድ መሪ፣ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
61መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
62በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
63ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
64ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
65ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የጋዲዮን ልጅ የአቢዳን. መስዋዕት ነበር፡፡
66በአስረኛው ቀን፣ የዳን ትውልድ መሪ፣ የአሚሳይ ልጅ አኪዔዘር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
67መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
68በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
69ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
70ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
71ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡
72በአስራ አንደኛው ቀን፣ የአሴር ትውልድ መሪ፣ የኤክራን ልጅ ፋግኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
73መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
74በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
75ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
76ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
77ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤክራን ልጅ የፋግኤል መስዋእት ነበር፡፡
78በአስራ ሁለተኛው ቀን፣ የንፍታሌም ትውልድ መሪ፣ የዔናን ልጅ ኢኬሬ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
79መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
80በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
81ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
82ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
83ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤናን ልጅ የኤኪሬ መስዋዕት ነበር፡፡
84የእስራኤል መሪዎች ሙሴ መሰዊያውን በቀባበት ቀን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አቀረቡ፡፡ አስራ ሁለት የብር ሳህኖች፣ አስራ ሁለት የብር ጎድጓዳ ሳህኖች እና አስራ ሁለት የወርቅ ሰሃኖች አቀረቡ፡፡
85እያንዳንዱ የብር ሳህን 130 ስቅሎች ሲመዝን እያንዳንዱ ጎድጓዳ ሰሀን ሰባ ሰቅሎች ይመዝናል፡፡ ሁሉም የውሃ መያዣዎች በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 2400 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡
86አስራ ሁለቱ ዕጣን የተሞሉ የወርቅ ሰሃኖች እያንዳንዳቸው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አስር ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡ ሁሉም የወርቅ ሳህኖች 120 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡
87ለሚቃጠል መስዋዕት አስራ ሁለት በሬዎች፣ አስራ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች አቀረቡ፡፡ የእህል ቁርባናቸውን ሰጡ፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት አስራ ሁለት ወንድ ፍየሎች ሰጡ፡፡
88ከብቶቻቸው ሁሉ፣ ሀያ አራት በሬዎች፣ ስልሳ አውራ በጎች፣ ስልሳ ወንድ ፍየሎች እና አንድ አመት የሆናቸው ስልሳ ወንድ ጠቦት በጎች የህብረት መስዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡ እነዚህ ሁሉ መሰዊያውን ለመቀደስ በሚቀባበት ጊዜ የቀረቡ ስጦታዎች ናቸው፡፡
89ሙሴ ከያህዌ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ድምጹን ሰማ፡፡ ያህዌ ከማስተሰርያ መክደኛ በላይ ሆኖ በቃል ኪዳን ታቦቱ ላይ፣ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ለእርሱ ተናገረ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።