መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ናዝራዊ ሆኖ ራሱን ለያህዌ በተለየ ስዕለት ሲለይ፣
3ከወይንና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፡፡ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የተሰራ ኮምጣጤ አይጠጣ፡፡ ማናቸውንም የወይን ጭማቂ አይጠጣ ወይም የወይን ፍሬ ወይም ዘቢብ አይብላ፡፡
4ለእኔ በተለየባቸው ቀናት ሁሉ፣ ከፍሬያቸው ግልፋፊ የተሰራ ማናቸውንም ነገር ጨምሮ ከወይን የተሰራ ምንም ነገር አይብላ፡፡
5ለያህዌ ራሱን የለየባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ በስለቱ ጊዜያት ሁሉ ራሱን ምላጭ አይንካው፡፡ ለያህዌ የተለየ ይሁን፡፡ ፀጉሩ በራሱ ላይ እንዲያድግ ይተወው፡፡
6ራሱን ለያህዌ በለየባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ወደ ሞተ ሰው አይቅረብ፡፡
7አባቱ፣ እናቱ፣ ወንድሙ ወይም እህቱ ቢሞቱ እንኳን ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡ ይህም የሚሆነው ማንም ሰው በረጅም ጠጉሩ እንደሚመለከተው፣ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው፡፡
8በተለየበት ጊዜ ሁሉ ለያህዌ የተለየ ቅዱስ ነው፡፡
9አንድ ሰው ድንገት አጠገቡ ቢሞት እና ማንነቱን የለየበትን ፀጉሩን ቢያረክስበት፣ መንጻት ባለበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ ራሱን ይላጭ፡፡ ራሱን መላጨት ያለበት በዚያን ጊዜ ነው፡፡
10በስምተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ያቅርብ፡፡
11ካህኑ አንዱን ወፍ ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን የሚቃተል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ሬሳ አጠገብ በመሆን ኃጢአት ሰርቷልና እነዚህ ለእርሱ ስርየት ይቀርባሉ፡፡ በዚያው ዕለት ራሱን መልሶ ለያህዌ ይስጥ፡፡
12ለተለየበት ጊዜ ራሱን ለያህዌ መልሶ ይስጥ፡፡ ለበደል መስዋዕት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት ያምጣ፡፡ ራሱን ከማርከሱ በፊት የነበሩ ቀናት አይቆጠሩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ተለይቶ ባለበት ጊዜ ረክሷል፡፡
13ናዝራዊ መለየቱ ስለሚያበቃበት ጊዜ የተሰጠው ህግ ይህ ነው፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያምጡት፡፡
14መስዋዕቱን ለያህዌ ያቅርቡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ለህብረት መስዋዕት ነውር የሌለበት አውራ በግ ያምጣ፡፡
15እንደዚሁም እርሾ ያልገባበት አንድ መሶብ ዳቦ፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ዳቦዎች፣ በዘይት የተቀባ እርሾ የሌለበት የገብስ ቂጣ፣ ከእህል ቁርባንና ከመጠጥ መስዋዕቶች ጋር ያምጣ፡፡
16ካህኑ እነዚህን በያህዌ ፊት ያቅርባቸው፡፡ እርሱ የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ያቅርብ፡፡
17ለያህዌ የህብረት መስዋዕቱን፣ እርሾ ካልገባበት ከመሶቡ ዳቦ ጋር፣ አውራ በጉን መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ እንዲሁም ካህኑ የእህል ቁርባኑን እና የመጠጥ መስዋዕቱን ጭምር ያቅርብ፡፡
18ናዝራዊው ለእግዚአብሔር መለየቱን የሚያሳየውን ፀጉሩን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጭ፡፡ ፀጉሩን ከራሱ ወስዶ የህብረት መስዋዕቶቹ በሚቀርቡበት በሚነደው እሳት ውስጥ ይጨምረው፡፡
19ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፣ ከመሶቡ ውስጥ እርሾ ያልገባበትን አንድ ዳቦ፣ እና አንድ እርሾ ያልገባበት የገብስ ቂጣ ይውሰድ፡፡ ናዝራዊው መለየቱን የሚያሳየውን ጸጉሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ እነዚህን በእጆቹ ያስይዘው፡፡
20ካህኑ እነዚህን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ከፍ አድርጎ ያንሳቸውና ለእርሱ ያቅርባቸው፡፡ ይህ ከፍ ተደርጎ ከተነሳው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋር ለካህኑ ተለየ ቅዱስ ምግብ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል፡፡
21ለያህዌ ለመለየት ስዕለቱን ያቀረበ ናዝራዊ ህጉ ይህ ነው፡፡ ማናቸውንም ሌሎች ነገሮች ቢሰጥ በናዝራዊነት ህግ መሠረት እንዲጠብቃቸው የተሰጡትን ቃል ኪዳኖች ለመጠበቅ የገባውን የስዕለት ግዴታዎች መጠበቅ አለበት፡፡”
22ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣
23“ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ ‘የእስራኤልን ሰዎች በዚህ መንገድ ባርኳቸው፡፡ እንደዚህ በሏቸው፣
24“ያህዌ ይባርችሁ ይጠብቃችሁ፡፡
25ያህዌ ብርሃኑን በእናንተ ላይ ያብራራ ፊቱን ይመልስላችሁ፣ ይራራላች፡፡
26ያህዌ በሞገስ ያጥግባችሁ፣ ሰላምንም ይስጣችሁ፡፡’”
27ለእስራኤል ሕዝብ ስሜን የሚያስተዋውቁት በዚህ መንገድ ነው፡፡ እኔም እባርካቸዋለሁ፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።