1ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንዲህ አላቸው፡፡
2“ከሌዋውያን መሃል የቀዓት ትውልዶችን ወንዶችን፣ በነገድ እና በየአባቶቸው ቤተሰቦች ቁጠሩ፡፡
3ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይምጡ፡፡
4የቀዓት ትውልድ በመገናኛው ድንኳን ለእኔ የተለዩትን እጅግ ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ይጠብቁ፡፡
5ህዝቡ ጉዞውን ለመቀጠል ሲነሳ፣ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳን ውስጥ ይግቡ፣ ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን የሚለየውን መጋረጃ ያውርዱት፣ ከዚያም የቃልኪዳኑን ታቦት ምስክር በእርሱ ይሸፍኑት፡፡
6ታቦቱን በአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑት፡፡ በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑት፡፡ ለመሸከም ምሰሶ ያስገቡበት፡፡
7በህብስት ማቅረቢያው ጠረጴዛ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉበት፡፡ በላዩ ድስቶቹን፣ ማንኪያዎችን እና ለመቅጃ ገንቦ ያስቀምጡበት፡፡
8በጠረጴዛው ላይ ህብስት አይታጣ፡፤ በደማቅ ቀይ ጨርቅ እና እንደገና በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኗቸው፡፡ ጠረጴዛውን ለመሸከም ምሰሰዎች ያስገቡ፡፤
9ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው የመቅረዝ መያዣውን ይሸፍኑ፣ ከመብራቶቹ ጋር፣ መቆንጠጫ፣ ዝርግ ሰሃኖች፣ እና ለመብራቶቹ የዘይት ገንቦዎችን ይውሰዱ፡፡
10መቅረዞቹንና መገልገያዎቹን በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያድርጉ፣ ከዚያም በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡቱ፡፡
11በወርቅ መሰዊያው ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉ፡፤ እርሱንም በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኑት፣ ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡
12ዕቃዎቹን ሁሉ ለሥራ ወደተቀደሰው ስፍራ ይውሰዱና በሰማያዊ ጨርቅ ይጠቅልሉ፡፡ በአስቆጣ ቁርበት ሸፍነው ዕቃዎቹን በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡ፡፡
13ከመሰዊያው አመዱን ያራግፉና ሐምራዊ ጨርቅ በመሰዊያው ላይ ያንጥፉ፡፡
14በመሰዊያው ላይ የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ በመሸከሚያው መሎጊያ ላይ ያስቀምጡ፡፡ እነዚህ ዕቃዎች፣ የእሳት ማንደጃዎች፣ ሜንጦዎች የእሳት መጫሪያዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና ለመሰዊያው የሚያገለግሉ ሌሎች መሳሪያዎች ናቸው፡፡ መሰዊያውን የአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑትና ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡
15አሮንና ልጆቹ ቅዱሱን ስፍራና መገልገያዎቹን ሙሉ ለሙሉ ሸፍው ሲጨርሱ፣ እና ህዝቡ ወደፊት ሲንቀሳቀስ በዚያን ጊዜ የቀዓት ትውልዶች ቅዱሱን ስፍራ ለመሸከም ይቅረቡ፡፡ የተቀደሱ ዕቃዎችን ከነኩ ይገደሉ፡፡ የቀዓት ትውልዶች የሥራ ድርሻ በመገናኛው ድንኳን የሚገኙ መገልገያዎችን መሸከም ነው፡፡
16የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ለመብራት የሚሆነውን ዘይት ያዘጋጃል፡፡ የጣፋጩን እጣን ዝግጅት ይቆጣጠራል፣ መደበኛውን የእህል ቁርባን፣ የቅባት ዘይቱን፣ ጠቅላላውን ቤተ መቅደስ እና በውስቱ ያሉትን ሁሉ፣ እንዲሁም በቅዱስ መገልገያዎችና ቁሳቁሶች ላይ ሀላፊነት ይኖረዋል፡፡”
17ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
18“የቀዓት የጎሳ ነገዶች ከሌዋዊያን መሃል እንዲወገዱ አትፍቀዱ፡፡
19በህይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ ይህን በማድረግ ጠብቋቸው፡፡ እጅግ ወደ ተቀደሱ ነገሮች ሲቀርቡ 20ለአፍታ እንኳን የተቀደሰውን ስፍራ ለማየት ወደ ውስጥ አይግቡ፣ አሊያ ይሞታሉ፡፡
20አሮንና ልጆቹ ወደ ውስጥ ይግቡ፣ ከዚያ አሮንና ልጆቹ ለእያንዳንዱ ቀዓታዊ የሚሰራውን ሥራ ይስጡት፣ ለእያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ተግባራት ይስጧቸው፡፡
21ያህዌ እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፣
22“ጌድሶናውያንንም በአባቶቻቸው ቤተሰቦች፣ በየነገዳቸው ቁጠራቸው፡፡
23ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ማገልገል የሚችሉትን ሁሉ ቁጠራቸው፡፡
24የጌድሶናውያን ነገዶች ሲያገለግሉና ሲሸከሙ ተግባራቸው ይህ ነው፡፡
25የመቅደሱን መጋረጃዎች ይሸከሙ፣ የመገናኛውን ድንኳን፣ መሸፈኛውን፣ በላዩ ላይ የሚገኘውን የአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ እና ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑትን መገረጃዎች ይሸከሙ፡፡
26የአደባባዩን መጋረጃ ይሸከሙ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፣ በቤተ መቅደሱና በመሰዊያው አጠገብ ያሉትን፣ ገመዶቻቸውን፣ ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ ይሸከሙ፡፡ በእነዚህ ነገሮች መደረግ ያለበትን ሁሉ፣ እነርሱ ያድርግ፡፡
27አሮንና ልጆቹ የጌድሶናውያን ትውልዶች ማገልገል ያለባቸውን አገልግሎት ይምሯቸው፡፡ በሚያጓጉዟቸው ነገሮች ሁሉ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻቸው ይምሯቸው፡፡ ያለባቸውን ሀላፊነቶች ሁሉ ትሰጧቸዋላችሁ፡፡
28ለመገናኛው ድንኳን የጌድሶናዊያን ነገድ ትውልዶች አገልግሎት ይህ ነው፡፡ የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታምር በአገልግሎታቸው ይምራቸው፡፡
29የሜራሪ ትውልዶችን በነገዳቸው ቁጠራቸው፣ በአባቶቻቸው ቤተሰቦችም እዘዛቸው፣
30ከሰላሳ አመት እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠር፡፡
31በመገናኛው ድንኳን የሚሰጧቸው አገልግሎቶችና የሥራ ድርሻቸው ይህ ነው፡፡ ቤተ መቅደሱን ለማስጌጥ እንክብካቤ ያድርጉ፣ የድንኳኑን ወርዶችና ቋሚዎች እና ካስማዎች ይሸከማሉ፣
32በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከሚገኙ ቋሚዎች ጋር፣ ችካሎቻቸውን፣ ካስማዎችን እና ገመዶቻቸውን ከተለያዩ መገልገያዎች ጋር ይሸከማሉ፡፡ መሸከም ያለባቸውን ቁሶች በስም ዘርዝር፡፡
33የሜራሪ ነገድ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር መሪነት በመገናኛው ድንኳን የሚሰጡት አገልግሎት ይህ ነው፡፡”
34የማህበሩ መሪ የሆኑት ሙሴና አሮን የቀዓታውያንን ትውልዶች በአባቶቻቸው ቤተሰቦች ነገዶች ቁጠሯቸው፡፡
35ሰላሳ አመት ዕድሜ የሞላቸውንና ከዚያ በላይ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠሯቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠሯቸው፡፡
36በየነገዳቸው 2750 ወንዶች ቁጠሩ፡፡
37ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ቀዓታዊያንን ወንዶች ሁሉ በየነገዳቸውና በየቤተሰባቸው ቁጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡
38የጌድሶናውያን ትውልዶች በየነገዳቸው፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣
39ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡
40በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 2630 ነበሩ፡፡
41ሙሴና አሮን በመገናኛው ድኗን የሚያገለግሉትን የጌድሶናውያንን ነገዶች ትውልዶች ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡
42የሜራሪያውያን ትውልዶች፣ በየነገዳቸውና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣
43ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡
44በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 3200 ነበሩ፡፡
45ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉትን የሜራሪ ትወልዶች የሆኑትን እነዚህን ወንዶች ሁሉ ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡
46ስለዚህም ሙሴ፣ አሮን፣ እና የእስራኤል መሪዎች ሁሉንም ሌዋውያን በየነገዳቸው በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ቆጠሯቸው
47ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቆጠሯቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ ማገልገል የሚችሉትን፣ እና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎችን መንከባከብና መሸከም የሚችሉትን እያንዳንዳቸውን ቆጠሯቸው፡፡
48በጠቅላላው 8580 ወንዶች ቆጠሩ፡፡
49በያህዌ ትዕዛዝ፣ ሙሴ እያንዳንዱን ወንድ ቆጠረ፣ እያንዳንዱን በተሰጠው የሥራ አይነት መሰረት ቆጠረ፡፡ እያንዳዱን ሰው በሚሸከመው ሀላፊነት አይነት ቆጠረ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን በመስራት ያህዌ ያዘዘውን አደረጉ፡፡