መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 34

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የእናንተ ወደምትሆን የከነዓን ምድርና ወደ ድንበሮቿ ስትገቡ፣
3ደቡባዊ ድንበራችሁ ከሲና ምድረ በዳ እስከ ኤዶም ይደርሳል፡፡ የደቡባዊ ድንበር ምስራቃዊ ጫፍ በጨው ባህር ደቡባዊ ጫፍ ድረስ ይሆናል፡፡
4ከአቅራቢም ኮረብታ ድንበራችሁ ወደ ደቡብ ይዞርና በሲና ምድረበዳ በኩል ያልፋል፡፡ ከዚያ ተነስቶ፣ በቃዴስ በርኔ ደቡብ ያልፍና ወደ ሐጸር አዳር እና ርቆ ዓጽምን ይደርሳል፡፡
5ከዚያ ተነስቶ፣ ድንበሩ ከጽሞን ወደ ግብጽ ጅረት ዞሮ እስከ ባህሩ ይከተለዋል፡፡
6ምዕራባዊው ድንበር የታላቁ ባህር ዳርቻ ይሆናል፡፡ ይህ ምዕራባዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡
7ሰሜናዊ ድንበራችሁ ከታላቁ ባህር እስከ ሆር ተራራ እስከ ምትይዙት ስፍራ ድረስ ይሰፋል፣
8ከዚያ ከሖር ተራራ እስከ ሌና ሐማት፣ ከዚያ እስከ ጽዳድ ይደርሳል፡፡
9ከዚያ ድንበሩ እስከ ዚፍሮን ይቀጥልና ሐጻር ዔርን ሲደርስ ይጨርሳል፡፡ ይህ ሰሜናዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡
10ምስራቃዊ ድንበራችሁን ከሐጸር ዔናን በደቡብ እስከ ሴፋም ታደርጋላችሁ፡፡
11ምስራቃዊ ድንበራችሁ ታች እስከ ሴፋም ወርዶ በዓይን ምስራቅ በኩል ራብላ ይደርሳል፡፡ ድንበሩ እስከ ከኔሬት ባህር ምስራቅ ይዘልቃል፡፡
12ከዚያ ድንበሩ በደቡብ በዮርዳኖስ ወንዝ በኩል እስከ ጨው ባህር እና ታች የጨው ባህር ምስራቅ ዳርቻ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህች ድንበሩን ተከትሎ ዙሪያውን በሙሉ የእናንተ ምድራችሁ ናት፡፡
13ሙሴ የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ሲል አዘዘ፣ “ያህዌ ለዘጠኙ ጎሳዎችና ለአንዱ ጎሳ እኩሌታ እንዲሰጣችሁ ያዘዘው፣ በዕጣ የምትካፈሏት ምድር ይህች ናት፡፡
14የሮቤል ጎሣ ትውልዶች እና የጋድ ጎሣ ትውልዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በየአባቶቻቸው ጎሣዎች የንብረት አከፋፈልን ስርዓት ተከትለው ርስታቸውን ተቀብለዋል፡፡
15ሁለቱ ጎሣዎችና የአንዱ ጎሣ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወዲያ በኢያሪኮ በስተ ምስራቅ በጸሀይ መውጫ የርስታቸውን ድርሻ ተቀብለዋል፡፡”
16ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣
17“ምድሪቱን ርስታችሁ አድርገው የሚያፋፍሏችሁ ሰዎች ስማቸው እነዚህ ናቸው፡ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፡፡
18ለየጎሣቸው ምድሪቱን እንዲያካፍሉ ከየነገዱ አንድ መሪ ምረጡ፡፡
19የሰዎቹም ስሞች እነዚህ ናቸው፡ ከይሁዳ ነገድ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፡፡
20ከስምኦን ጎሣ ትውልዶች የዓሁድ ልጅ ሰላሚኤል፡፡
21ከቢኒያም ጎሣ፣ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፡፡
22መሪ ከሆነው ከዳን ጎሣ ትውልዶች፣ የዩግሊ ልጅ ቡቂ፡፡
23ከዮሴፍ ትውልዶች፣ መሪ ከሆነው ከምናሴ ትውልዶች የሱፊድ ልጅ አኒኤል፡፡
24መሪ ከሆነው ከኤፍሬም ጎሣ ትውልዶች፣ የሺፍጣን ልጅ ቱሙኤል፡፡
25መሪ ከሆነው ከዛብሎን ጎሣ ትውልዶች የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፡፡
26መሪ ከሆነው ከይሳኮር ጎሣ ትውልዶች፣ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፡፡
27መሪ ከሆነው ከኤሴር ጎሣ፣ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፡፡
28መሪ ከሆነው ከንፍታሌም ጎሳ ትውልዶች፣ የዓሚሁድ ልጅ ፈዳሄል” ናቸው፡፡
29ያህዌ እነዚህን ሰዎች የከነዓንን ምድር እንዲያካፍሉና ለእያንዳንዱ የእስራኤል ጎሣዎች ድርሻቸውን እንዲሰጡ አዘዘ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።