1የእስራኤል ህዝብ በሙሴና አሮን መሪነት በየታጣቂ በድኖቻቸው ሆነው ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ ያደረጓቸው ጉዞዎች እነዚህ ነበሩ፡፡
2ሙሴ በያህዌ እንደታዘዘው፣ ከተነሰቡት አንስቶ እስሚሄዱበት ድረስ ያሉትን ስፍራዎች ጻፈ፡፡ ከስፍራ ስፍራ ያደረጓቸው እንቅስቃሴዎች እነዚህ ነበሩ፡፡
3በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አምስተኛ ቀን ከራምሴ ተነስተው ተጓዙ፡፡ ከፋሲካው በኋላ በማለዳ፣ የእስራኤል ሕዝብ በግልጽ ግፃዊያን ሁሉ እያይዋቸው ወጡ፡፡
4ግብፃዊያን ያህዌ በመካከላቸው የገደላቸውን በኩሮቻቸውን እየቀበሩ ሳለና በአማልክቶቻቸው ላይ ጥፋት እያደረሰ ሳለ ይህ ሆነ፡፡
5የእስራኤል ሕዝብ ከራምሴ ወጥቶ በሱኮት ሰፈረ፡፡
6ከሱኮት ወጥተው በኤታሞ፣ በምድረ በዳው
7ከኤታም ወጥተው ከበአልዛፎን በተቃራኒ ወደ ፊሀሔርት ተመልሰው በሚግዶል በተቃራኒ ሰፈሩ፡፡
8ከዚያም ከፈሀሔርት በተቃራኒ ተነስተው በባህሩ መሃል ወደ ምድረበዳው ሄዱ፡፡ ለሶስት ቀናት በኤታም ምድረ በዳ ተጉዞው በማራ ሰፈሩ፡፡
9ከማራ ተነስተው ኤሊም ደረሱ፡፡ በኤሊም አስራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የቴምር ዛፎች ነበሩ፡፡ የሰፈሩት በዚያ ስፍራ ነው፡፡
10ከኤሊም ተነስተው ቀይ ባህር አጠገብ ሰፈሩ፡፡
11ከቀይ ባህር ተነስተው በሲን ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡
12ከሲን ምድረበዳ ተነስተው በራፍቃ ሰፈሩ፡፡
13ከራፍቃ ተነስተው በኤሉስ ሰፈሩ፡፡
14ከኤሉስ ተነስተው የሚጠጣ ውሃ በሌለበት ሰራፊዲም ሰፈሩ፡፡
15ከራፊዲም ተነስተው በሲና ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡
16ከሲና ምድረበዳ ተነስተው በቂብሮት ሃታቫ ሰፈሩ፡፡
17ከቂብሮት ሃታቫ ተነስተው በሐዴሮት ሰፈሩ፡፡
18ከሐዴሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ፡፡
19ከሪትማ ተነስተው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ፡፡
20ከሬምን ዘፋሬስ ተነስተው በልብና ሰፈሩ፡፡
21ከልብና ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ፡፡
22ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ፡፡
23ከቀሄላታ ተነስተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ፡፡
24ከሻፍር ተራራ ተነስተው በሐራዳ ሰፈሩ፡፡
25ከሐራዳ ተነስተው በመቅሄሎት ሰፈሩ፡፡
26ከመቅሄሎት ተነስተው በታሐት ሰፈሩ፡፡
27ከታሐት ተነስተው በታራ ሰፈሩ፡፡
28ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ፡፡
29ከሚትቃ ተነስተው በሐሹምና ሰፈሩ፡፡
30ከሐሽምና ተነስተው በምሴሮት ሰፈሩ፡፡
31ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ፡፡
32ከብኔያዕቃን ተነስተው በሖር ሃጊድጋድ ሰፈሩ፡፡
33ከሖር ሃጊድጋ ተነስተው በዮጥባታ ሰፈሩ፡፡
34ከዮጥባታ ተነስተው በዔብሮና ሰፈሩ፡፡
35ከዔብሮና ተነስተው በዔድዮን ጋብር ሰፈሩ፡፡
36ከዔድዮን ጋብር ተነስተው በቃዴስ በምትገኘው ጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡
37ከቃዴስ ተነስተው በሖር ተራራ፣ በኤዶም ምድር ዳርቻ ሰፈሩ፡፡
38ካህኑ አሮን፤ በያህዌ ትዕዛዝ ወደ ሖር ተራራ ወጣ፣ የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን በዚያ ሞተ፡፡
39አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት ዕድሜው 123 ነበር፡፡
40በከነዓን ምድር በደቡባዊ በረሃ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉስ የእስራኤልን ህዝብ መምጣት ሰማ፡፡
41እነርሱ ከሖር ተራራ ተነስተው በሴልምና ሰፈሩ፡፡
42ከሴልምና ተነስተው በፋኖን ሰፈሩ፡፡
43ከፋኖን ተነስተው በአቦት ሰፈሩ፡፡
44ከአቦት ተነስተው በሞአብ ዳርቻ በኢየ አባሪም ሰፈሩ፡፡
45ከኢየ አባሪም ተነስተው በዲቦን ጋድ ሰፈሩ፡፡
46ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡ 46ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡
47ከዓልምን ዲብላታይም ተነስተው ከናባው ተራራ በተቃራኒ በዓብሪም ተራራ ሰፈሩ፡፡
48ከዓብሪም ተራራ ተነስተው በሞብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪኮ ላይ ሰፈሩ፡፡
49በሞብ ሞአብ ዮርዳስ ላይ ከቤት የሺሞት እስከ አቤልስጢም ድረስ ሰፈሩ፡፡
50ያህዌ ሙሴን በሞአብ ሜዳዎች ዮርዳስ ውስጥ በኢያሪኮ ሳለ እንዲህ አለው፣
51“ለእስራኤላዊያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ዮርዳኖስን አቋርጣችሁ ወደ ከነዓን ስትገቡ፣
52የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አስወጡ፡፡ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን በሙሉ አጥፉ፡፡ የማምለኪያ ስፍራዎቻቸውንና የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ሁሉ ደምስሱ፡፡
53የምድሪቱን ሀብት ውሰዱ በዚያም መኖር ጀምሩ፣ ምክንያቱም እኔ ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቻቸኋለሁ፡፡
54ምድሪቱን በእጣ እንደየ ጎሳው ብዛት ውረሱ፡፡ ብዙ ህዝብ ላለው ጎሳ ሰፊ መሬት ስጥ፣ አነስተኛ ቁጥር ላለው ጎሳ አነስ ያለ መሬት ስጥ፡፡ እያንዳንዱ ጎሳ እጣው በወደቀለት ስፍራ ያ መሬት ርስቱ ይናል፡፡ ምድሪቱን በአባቶችሁ ጎሳ መሰረት ትወርሳላችሁ፡፡
55የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ጨርሳችሁ ባታስወጡ ግን፣ እንዲቀሩ ያደረጋችኋቸው ሰዎች በዐይናችሁ ውስጥ እንደገባ ባዕድ አካል እና በጎናችሁ እንደገባ እሾህ ይሆኑባችኋል፡፡ በመትኖሩበት ምድር ሕይወታችሁን ከባድ ያደርጉባችኋል፡፡
56እኔ በእነዚህ ህዝቦች ላይ ላደርስባቸው ያቀድኩትን በእናንተም ላይ ደግሞ አደርገዋለሁ፡፡’”