መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 32

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በዚህ ጊዜ የሮቤልና የጋድ ትውልዶች ብዙ የቀንድ ከብቶች ነበራቸው፡፡ የኢያዜርንና የገለዓድን ምድር ሲመለከቱ፣ ምድሪቱ ለከብቶቻቸው መልካም መሆኗን አዩ፡፡
2ስለዚህ የጋድና ሮቤል ትውልዶች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛርና ወደማህበሩ መሪዎች መጥተው እንዲህ አሉ፣
3“ያህዌ በእስራኤል ህዝብ ፊት የመታው አጣሮት፣ ዲቦን ኢያዜር፣ ኒምራ፣ ሐሴናን፣ ኤልያሊ፣ ሴባማ፣ ናባውና ባያን
4ምድሩ ለከብቶች መልካም ነው፡፡ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ብዙ ከበቶች አሉን፡፡”
5ደግሞም እንዲህ አሉ፣ “በፊትህ ሞገስ አግኝተን ከሆነ፣ ይህች ምድር ለእኛ ለአገልጋዮችህ ርስት ሆና ትሰጠን፡፡ ዮርዳኖስን አቋርጠን እንድንሄድ አታድርግ፡፡”
6ሙሴ ለጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እናንተ በዚህ ተቀምጣችሁ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሊሄዱ ይገባልን?
7የእስራኤል ህዝብ ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ለምን ልባቸውን ታደክማላችሁ?
8አባቶቻችሁ ከቀዴስ በርኔ ምድሪቱን እንዲያዩ በላክኋቸው ጊዜ ያደረጉት ተመሳሳይ ነገር ነበር፡፡
9እነርሱ ወደ ኤሽኮል ሸለቆ ሄዱ፡፡ ምድሪቱን ካዩ በኋላ የእስራኤልን ልብ አደከሙ፤ ስለዚህም ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር ለመግባት ተቃወሙ፡፡
10በዚያ ቀን የያህዌ ቁጣ ነደደ፡፡ በመሀላ እንዲህ አለ፣
11‘ከግብጽ ምድር ከወጡ ሰዎች ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ከሆናቸው፣ መሃል አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ፣ እና ለያዕቆብ ልሰጣቸው በመሀላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩም፣ ምክንያቱም እነርሱ በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤
12ከቂኔዛዊው ከዩፎኒ ልጅ ከካሌብ፣ እና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር፡፡ ካሌብና ኢያሱ ብቻ በሙሉ ልባቸው ተከትለውኛል፡፡’
13ስለዚህም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡ በፊቱ ክፉ ያደረገው ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ ለአርባ አመታት በምድረበዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው፡፡
14እናንተ እንደ ሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች የያህዌን ቁጣ በእስራኤል ላይ ለመጨመር በአባቶቻችሁ እግር ተተካችሁ፡፡
15እርሱን ከመከተል ፊታችሁን ብታዞሩ፣ እርሱ እስራኤልን ዳግም በበረሃ ይተዋል እናንተም ይህን ሁሉ ህዝብ ታጠፋላችሁ፡፡”
16ስለዚህም ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “በዚህ ለከብቶቻችን አጥር እና ለቤተሰቦቻችን ከተማ እንድንገነባ ፍቀድል፡፡
17ሆኖም፣ እኛ እራሳችን ወደ ስፍራቸው እስክናባርራቸው ድረስ ከእስራኤል ጦር ጋር ለመውጣት እንነሳለን እንታጠቃንም፡፡ ቤተሰቦችን ግን እስከ አሁን በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሌሎች ሰዎች የተነሳ በተቀጠሩ ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ፡፡
18የእስራኤል ህዝብ እያንዱ ሰው ርስቱን እስኪያገኝ ድረስ ወደ ቤቶቻችን አንመለስም፡፡
19እኛ ከእነርሱ ጋር ከዮርዳኖስ ማዶ ያለውን ምድር አንወርስም፣ ምክንያቱም የእኛ ርስት እዚህ በዮርዳኖስ ምስራቅ በኩል ያለው ነው፡፡”
20ስለዚህም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “የተናገራችሁትን ካደረጋችሁ፣ ወደ ጦርነት በያህዌ ፊት ለመውጣት ራሳችሁን ካስታጠቃችሁ፣
21ከዚያ በኋላ እያንዳንዳቸው የእናንተ የታጠቁ ወንዶች ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያባርራቸው ድረስ በያህዌ ፊት ዮርዳኖስን ማቋረጥ አለባቸው፡፡
22ደግሞም ምድሪቱ በእርሱ ፊት ጸጥ ብላ ትገዛለች፡፡ ከዚያ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፡፡ እናንተም በያህዌና በእስራኤል ፊት ጥፋተኛ አትሆኑም፡፡ ይህ ምድር በያህዌ ፊት ርስታችሁ ይሆናል፡፡
23እንዲህ ካላደረጋችሁ ግን፣ በያህዌ ፊት በደለኞች ትሆናላችሁ ኃጢአታችሁ እንደሚከተላችሁ እርግጠኞች ሁኑ፡፡
24ለቤተሰቦቻችሁ ከተሞችን ገንቡ ለበጎቻችሁም ጉረነዎች ስሩላቸው፤ ከዚያ ያላችሁትን አድርጉ፡፡”
25የጋድና ሮቤል ትውልዶች ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “እኛ አገልጋዮችህ አንተ ጌታችን ያዘዝከንን እናደርጋለን፡፡
26ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ መንጎችንና የቀን ከብቶቻችን በገለዓድ ከተሞች ይቆያሉ፡፡
27ሆኖም፣ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ለጦርነት በያህዌ ፊት እንወጣን፤ ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ሰው አንተ ጌታችን እንዳልከው ያደርጋል፡፡”
28ስለዚህም ሙሴ ለካህኑ አልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል የጎሳዎች አባቶች ለሆኑ መሪዎች እነርሱን በሚመለከት መመሪያዎቻችን ሰጠ፡፡
29ሙሴ እንዲህ አላቸው፣ “የጋድና የሮቤል ትውልዶች ከእናንተ ጋር ዮርዳስን ቢሻገሩና በያህዌ ፊት ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ወንድ እና ምድሪቱ በፊታችሁ ቢገዙ፣ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ፡፡
30ነገር ግን ታጥቀው ከአንተ ጋር ዮርዳኖስን ባይሻገሩ፣ ርስታቸውን በከነአን ምድር ከአንተ ጋር ያገኛሉ፡፡”
31ስለዚህም የጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያህዌ ለእኛ ለባሮችህ እንደተናገረው፣ የምናደርገው ነገር ይህ ነው፡፡ እንሻገራለን፡፡
32እኛ ታጥቀን በያህዌ ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፣ ነገር ግን የተወረሰው ርስታችን በዚህኛው የዮርዳስ ክፍል ከእኛ ጋር ይቀራል፡፡”
33ስለዚህ ሙሴ ለጋድና ለሮቤል ትውልዶች፣ እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ከፊል ነገድ፤ የአሞውያንን ንጉስ የሴዎንን ግዛት እና የባሳንን ንጉስ የዓግን ግዛቶች ሰጣቸው፡፡ ለእነርሱ ምድሪቱን ሰጣቸው፣ እንዲሁም ከተማዎቿን ከዳርቻዎቻቸው ጋር እና በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችን አደላቸው፡፡
34የጋድ ትውልዶች ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣
35ዓጥሮት ሾፋንን፣ አያዜርን፣ ዮግብሃን፣
36ቤት ነምራንን እና ቤት ሃራንን የተቀጠሩ ከተሞችና ለበጎች ጉረኖዎች ያላቸው አድርገው እንደገና ገነቧቸው፡፡
37የሮቤል ትውልዶች ሐሴቦንንና፣ ኤልያሊንና ቂርያትይምን፣
38ናባውን፣ በአልሜዎንን (ስማቸው በኋላ ተቀይሯል) እና ሴባማንን እንደገና ገነቧቸው፡፡ እነርሱም ዳግም ለገነቧቸው ከተሞች ሌላ ስሞችን ሰጡ፡፡
39የምናሴ ልጅ የማኪር ትውልዶች ወደ ገለዓድ ሄደው በውስጧ ይኖሩ ከነበሩት ከአሞራውያን ከለአድን ወሰዱ፡፡
40ከዚያ ሙሴ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠው፣ የእርሱም ሰዎች መኖሪያችን በዚያ አደረጉ፡፡
41የምናሴ ልጅ ኢያዕር ሄዶ ከተማቸውን ይዞ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው፡፡
42ኖባህ ሄዶ ቄናትንና መንደሮቿን ይዞ፣ በራሱ ስም ኖባህ ብሎ ሰየማት፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።