1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“የእስራኤል ህዝብ ምድያማውያንን ይበቀሉ፡፡ ያን ካደረግህ በኋላ፣ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ፡፡”
3ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ እንዲህ አለ፣ “በምድያማውያን ላይ የያህዌን በቀል ይፈጽሙ ዘንድ ከወንዶቻችሁ አንዳንዶቹን ወደ ጦርነት እንዲወጡ አስታጥቋቸው፡፡
4እያንዳንዱ በእስራኤል ውስጥ ያለ ጎሳ ለጦርነት አንድ ሺህ ወታደሮችን መላክ አለበት፡፡”
5ስለዚህ ከእስራኤል ብዙ ሺህ ወንዶች መሀል ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሺህ ሰው ለጦርነት ቀረበ፣ በጠቅላላው አስራ ሁለት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡
6ከዚያ ሙሴ ከየጎሳው አንድ ሺህ ሰዎችን ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሃስ ጋር እና ከተቀደሰው ስፍራ ከጥቂት ቁሳቁሶችና እንዲሁም ምልክቶችን ለማሰማት በእጁ ያሉትን መለከቶች አስይዞ ወደ ጦርነት ላካቸው፡፡
7እነርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ከምድያማውያን ጋር ተዋጉ፡፡ ሰዎቹን ሁሉ ፈጇቸው፡፡
8የምድያምን ነገስታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር ሑርን እና እና ሪባን ከተቀሩት ጋር በሰይፍ ገደሏቸው፡፡
9የእስራኤል ጦር፤ የምድያምን ሴቶች፣ ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውን ሁሉ፣ መንጋዎቻቸውን እና ንብረቶቻቸውን ሁሉ ምርኮ አደረጉ፡፡ እዚህን ሁሉ ዘርፈው ወሰዱ፡፡
10የሚኖሩባቸውን ከተሞችና ሰፈሮች ሁሉ አቃጠሉ፡፡
11የሰውና እንስሳት ምርኮዎቻቸውንና እስረኞችን ወሰዱ፡፡
12እስረኞችን፣ የዘረፉትን፣ እና የያዙትን ነገሮች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛር፣ እና ወደ እስራኤል ማህበረሰብ አመጡ፡፡ እነርሱም እነዚህን ኢያሪኮ አጠገብ ዮርዳስ፣ በሞአብ ሜዳ ላይ ወደ ሚገኘው ሰፈር አመጡ፡፡
13ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ፡፡
14ሙሴ ግን ከጦርነት በተመለሱት በጦሩ መኮንኖች፣ በሻለቃዎችና በመቶ አለቆች ላይ ተቆጥቶ ነበር፡፡
15ሙሴ መኮንኖቹን እንዲህ አላቸው፣ “ሴቶቹ ሁሉ በህይወት እንዲኖሩ ተዋችኋቸውን?”
16እነዚህ ሴቶች በበለዓም ምክር፣ የእስራኤል ህዝብ በያህዌ ላይ በፌጎር ኃጢአት እንዲሰራና መቅሰፍት እንዲወርድበት ያደረጉ ናቸው፡፡
17ስለዚህ አሁን፣ ትናንሾቹን ወንዶች ሁሉ ግደሉ፣ ከወንድ ጋር የተኙ ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፡፡
18ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁትን ወጣት ልጃገረዶች ግን ለራሳችሁ ውሰዱ፡፡
19ከእስራኤል ሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት መቆየት አለባችሁ፡፡ ማንንም ሰው የገደላችሁ ሁሉና ወይም የሞተ ሰው የነካችሁ ሁሉ በሶስተኛው ቀንና በሰባተናው ቀን ራሳችሁን ማንጻት አለባችሁ፡፡ እናንተና ምርኮኞቻችሁ መንጻት አለባችሁ፡፡
20ልብሶቻችሁን አንጹ፣ ከእንስሳት ቆዳ እና ከፍየል ፀጉር የተሰሩ ማናቸውንም ነገሮች፣ እንዲሁም ከእንጨት የተሰሩ ነገሮችን ሁሉ አንጹ፡፡”
21ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነት የሄዱትን ወታደሮች እንዲህ አላቸው፣ “ይህ ያህዌ ለሙሴ የሰጠው የተደገነገገ ህግ ነው፡
22ወርቁ፣ ብሩ፣ ነሀሱ፣ ብረቱ፣ ቆርቆሮውና እርሳሱ
23እና ማናቸውም እሳት የሚቋቋምን ነገር በእሳት ውስጥ አሳልፉት እናም የተቀደሰ ይሆናል፡፡ እነዚያን ነገሮች በማንጻት ውሃ አንጹዋቸው፡፡ በእሳት ውስጥ ማለፍ የማይችለውን ማናቸውንም ነገር በውሃ አንጹ፡፡
24እናም ልብሶችሁን በሰባተኛው ቀን እጠቡ፣ ከዚያም የተቀደሳችሁ ትሆናላች፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ እስራኤል ሰፈር መግባት ትችላላችሁ፡፡”
25ከዚያም ያህዌ ሙሴን እንደዚህ አለው፣
26”ሰዎችም ይሁኑ እንስሳት፣ የተማረኩትንና የተወሰዱትን ነገሮች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ አንተ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች እንዲሁም የጎሳ አባቶች
27ምርኮዎቹን ለሁለት ክፍል ክፈሏቸው፡፡ ለጦርነት በወጡ ወታደሮችና በተቀረው ማህበረሰብ መሃል ምርኮውን አከፋፍሉ፡፡
28ከዚያ ወደ ጦርነት ከወጡ ወታደሮች ለእኔ የሚሰጥ ግብር ጣል፡፡ ይህ ግብር ከሰዎችም ይሁን፣ ከቀንድ ከብት፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ከየአምስት መቶው አንዱ ይሁን፡፡
29ይህን ግብር የእነርሱ ከሆነው ከከፊሉ ድርሻቸው ወስደህ ለእኔ የሚቀርብ ስጦታ እንዲሆን ለካህኑ አልዓዛር ስጠው፡፡
30ደግሞም ከከፊሉ የእስራኤል ህዝብ ድርሻ ከሆነው ሰዎች፣ ከቀንድ ከብቶች፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ከፍየሎች፣ ከየሀምሳው መሀል አንዱን ወሰድ፡፡ እነዚህን ማደሪያዬን ለሚያገለግሉት ለሌዋውያን ስጣቸው፡፡”
31ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡
32ወታደሮቹ በዝብዘው የወሰዱት ምርኮ 675000 በጎች፣
33ሰባሁለት ሺህ በሬዎች፣
34ስልሳ አንድ ሺህ አህዮች፣
35እና ሰላሳ ሁለት ሺህ ከወንድ ጋር ያልተኙ ሴቶች ነበሩ፡፡
36ለወታደሮች የተጠበቀላቸው ግማሹ 337000 በጎች ነበሩ፡፡
37ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 675 በጎች ነበር፡፡
38በሬዎቹ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሲሆኑ የያህዌ ግብር 72 ነበር፡፡
39አህዮች 30500 ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 61 ነበር፡፡
40ሰዎቹ አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ ለያህዌ የተሰጠው ግብር 32 ነበር፡፡
41ሙሴ ለያህዌ የሚቀርቡትን ስጦታዎች ግብር ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ለካህኑ አልዓዛር ይህንን ሰጠ፡፡
42ሙሴ ወደ ጦርት ከሄዱ ወታደሮች የወሰደውን የእስራኤል የሆነውን ግማሽ ምርኮ በተመለከተ፤
43የማህበረሰቡ ከምርኮ ግማሹ 337500 በጎች፣
44ሰላሳ ስድስት ሺህ በሬዎች፣
45ሰላሳ ሺ አምስት መቶ አህዮች፣
46እና አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፡፡
47ከእስራኤል ህዝብ ግማሽ ከሆነ ድርሻው፣ ሙሴ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት ከየአምሳው መሀል አንድ ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት የያህዌን ማደሪያ ለሚያገለግሉ ለሌዋውያን እነዚህን ሰጠ፡፡
48ከዚያ የሰራዊቱ መኮንኖች፣ የሻለቃ አዛዦች እና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ መጡ፡፡
49እንዲህም አሉ፣ “ባሮችህ በእኛ ስር ያሉትን ወታደሮች ቆጠርን፣ አንድ ሰው እንኳን አልጎደለም፡፡
50እኛ የያህዌን ስጦታ አምጥተናል፣ እያንዳንዱ ሰው ያገኘውን፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ አልቦዎችና አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጉትቻዎች፣ እና የአንገት ሀብሎች ማስተስረያ እንደሆነን በያህዌ ፊት አምጥተናል፡፡”
51ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁንና የእጁ ጥበብ ውጤት የሆኑትን የጌጥ ዕቃዎች ሁሉ ከእነርሱ ተቀበሉ፡፡
52ለያህዌ ያቀረቧቸው የወርቅ ስጦታዎች ሁሉ ከሻለቃዎችና ከመቶ አለቃዎች የተቀበሏቸው ስጦታዎች ክብደታቸው 16750 ሰቅሎቸ ነበር፡፡
53እያንዳንዱ ወታደርና እያንዳንዱ ሰው ከምርኮው ለራሱ ወስዷል፡፡
54ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወርቁን ወሰዱ፡፡ ለያህዌ የእስራኤል ህዝብ ማስታወሻ አድርገው ወርቁን ወደ መገናኛው ድንኳን አስገቡት፡፡