1”በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡ ይህ ቀን መለከቶችን የምትነፉበት ቀን ይሆናል፡፡
2ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡
3ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባናቸውን፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፤ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አራተኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ
4እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡
5ለኃጢአት ማስተስረያ አንድ ወንድ ፍየል አቅርቡ፡፡
6በየወሩ መጀመሪያ ከምታደርጉት የተለየ የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ፣ እነዚህን መስዋዕቶች በሰባተኛው ወር አድርጉ፡፡ እነዚህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት ከእህል ቁርባኑና የመጠጥ ቁርባኖች በተጨማሪ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ እነዚህን መስዋዕቶች ስታደርጉ፣ ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ የተደነገገውን ትፈጽማላችሁ፡፡
7በሰባተኛ ወር በአስረኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት ታዋርዳላችሁ በዕለቱ ሥራ አትሰሩም፡፡
8ለያህዌ ጣፋጭ ማዐዛ ያለው የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ሰባት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ይሁኑ፡፡
9ከዚህ ጋር የእህል ቁርባን፤ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ፣
10እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ ታቀርባላችሁ፡፡
11አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ማቅረበ አለባችሁ፡፡ ይህ ለኃጢአት ማስተስረያ፣ ለመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና ከእነዚህ ጋር በሚቀርበው የመጠጥ መስዋእቶች በተጨማሪ የሚቀርብ ነው፡፡
12በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፣ ደግሞም ለሰባት ቀናት ክብረ በዓሉን ለእርሱ ታደርጋላችሁ፡፡
13በእሳት የተዘጋጀ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት ማቅረብ አለባችሁ፡፡ አስራ ሶስት ወይፈኖች፣ እና የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው አስራ አራት ወንድ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ እያንዳንችው ነውር የሌለባቸው መሆን አለባቸው፡፡
14ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን፣ ለአስራ ሶስቱም ወይፈኖች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለሁለቱ አውራ በጎች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሁለት አስረኛ
15እና ለአስራ አራቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ፤ በዘይትየተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡
16ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት፤ ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
17በስብሰባው ሁለተኛ ቀን፣ አስራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
18ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
19ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
20በስብሰባው ሶስተኛ ቀን፣ አስራ አንድ ወይፈኖች ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
21ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
22ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
23በስብሰባው አራተኛ ቀን፣ አስር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
24ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች፣ ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
25ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
26በስብሰባው አምስተኛ ቀን፣ ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
27ከእነዚህም ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ፣ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
28ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
29በስበሰባው ስድስተኛ ቀን ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
30ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
31ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው እህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረበ አለባችሁ፡፡
32በስብሰባው ሰባተኛ ቀን፣ነውር የሌለባቸው፣ ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
33ከወይፈኖች፣ከአውራ በጎች እና ጠቦቶች ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ታቀርባላችሁ፡፡
34ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እንዲሁም ከመጠጥ ቁርባኑ በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
35በስብሰባው ስምንተኛ ቀን፣ ሌላ የከበረ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያን ቀን የተለመደ የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፡፡
36የሚቃጠል መስዋዕት ታደርጋላችሁ፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ያለው መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር ሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡
37ለወይፈኑ፣ ለአውራ በጉ፣ እና ለጠቦቶቹ የእህል ቁርባናቸውንና የመጠጥ ቀርባናቸውን በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትእዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
38ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
39በተወሰነ ክብረ በዓላቶቻችሁ ለያህዌ የምታቀርቧቸው እነዚህ ናቸው፡፡ እነዚህም ከስለቶቻችሁና የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው፡፡ እነዚህን የሚቃጠሉ መስዋዕቶቻችሁ፣ የእህል ቁርባኖች፣ የመጠጥ ቁርባኖች፣ እና የህብረት መስዋዕቶች አድርጋችሁ አቅርቧቸው፡፡”
40ሙሴ ያህዌ ለእስራኤል ሰዎች እንዲናገር ያዘዘውን ሁሉ ተናገረ፡፡