1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2”የእስራኤል ሰዎችን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘በወቅቱ ለእኔ መስዋዕቶችን አቅርቡ፣ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ያለው በእሳት የተበጀ መስዋዕት ለእኔ አቅርቡልኝ፡፡’
3ደግሞም እንዲህ በላቸው፣ ‘ይህ ለያህዌ የምታቀርቡት የእሳት መስዋዕት ነው፡፡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ጠቦት፣ እንደ መደበኛ መስዋዕት በእያንዳንዱ ቀን ሁለት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡
4አንዱን ጠቦት በማለዳ ታቀርባላችሁ፣ ሌላውን ጠቦት በምሽት ታቀርባላችሁ፡፡
5በተጠለለ የኢን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የአፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ አቅርቡ፡፡
6ይህ በሲና ተራራ የተደነገገ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ ያለው መደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡
7ከዚህ ጋር የሚቀርበው የመጠጥ መስዋዕት ለአንዱ ጠቦት የኢን አንድ አራተኛ ይሁን፡፡ በተቀደሰው ስፍራ ለያህዌ የመጠጥ ስጦታ አፍስሱ፡፡
8ሌላውን ጠቦት ከሌላ የእህል ቁርባን ጋር በማለዳ ባቀረባችሁት መስዋዕት አይነት በምሽት አቅርቡ፡፡ ከዚህ ጋር ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የተዘጋጀ ሌላ የመጠጥ መስዋዕትም አቅርቡ፡፡
9በሰንበት ቀን ነውር የሌላቸው ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች፣ እና በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ ከመጠጥ መስዋዕት ጋር አቅርቡ፡፡
10ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ በየሰንበቱ የሚቃጠል መስዋዕት እንዲሆን ነው፡፡
11በየወሩ መጀመሪያ፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እና ነውር የሌለባቸው ሰባት ወንድ የበግ ጠቦት መስዋዕት አድርጋችሁ አቅረቡ፡፡
12ለእያንዳዱ ወይፈን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፣ ደግሞም ከአውራ በጉ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
13እንደዚሁም ለእያንዳንዱ ጠቦት የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ የሚሰጥ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሆን ነው፡፡
14የሰዎች የመጠጥ ቁርባን ላንድ ኮርማ በሬ የኢን ግማሽ ወይን ጠጅ ይሁን፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢን አንድ ሶስተኛ፣ ለአንድ ጠቦት በግ የኢን አንድ አራተኛ ወይን ጠጅ ይሁን፡፡ ይህ አመቱን በሙሉ በእያንዳንዱ ወር የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡
15ለያህዌ አንድ ወንድ ፍየል የኃጢአት መስዋዕት መቅረብ አለበት፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርብ የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ነው፡፡
16በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን የያህዌ ፋሲካ ይውላል፡፡
17በዚህ ወር የአስራ አምስተኛው ቀን ክብረ በዓል ይሆናል፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ የሌለበት ቂጣ ይበላል፡፡
18በመጀመሪያው ቀን ያህዌን ለማክበር ቅዱስ ጉባኤ ይደረጋል፡፡ በዚያ ቀን የዘወትር ሥራችሁን አትሰሩም፡፡
19ሆኖም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ የሚቃጠል መስዋዕት ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ሰባት ወንድ የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፡፡
20ከወይፈኑ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢን ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን፣ ከአውራ በግ ጋር የኢን ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
21ከእያንዳንዳቸው ከሰባቱ ጠቦቶች ጋር፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፣
22እንዲሁም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ለማስተሰርያ አቅርቡ፡፡
23እነዚህን በየጠዋቱ ከሚያስፈልገው መደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት በተጨማሪ አቅርቡ፡፡
24እዚህ እንደ ተገለፀው፣ እነዚህን መስዋዕቶች በየቀኑ ማቅረብ አለባችሁ፣ በፈሲካ ሳምንት፣ በእሳት የተዘጋጀው የምግብ መስዋዕት ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይቅረብ፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ መቅረብ አለበት፡፡
25በሰባተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፣ ደግሞም በዚያ ቀን የየዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡
26እንደዚሁም በበኩራት ፍሬ ቀን፣ በክብረ በዓላችሁ ሳምንታት የአዲስ እህል ስጦታ ለያህዌ ስታቀርቡ፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን የተለመደ የየዕለት ተግባራችሁን አትስሩ፡፡
27ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ሰባት የአንድ አመት ጠቦት በጎች አቅርቡ፡፡
28ከእነዚህ ጋር እነዚህን የእህል ቁርባን አቅርቡ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለእያንዳንዱ ወይፈን የኢፍ ሶስት አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ እና ለአውራ በጉ ሁለት አስረኛ የእህለ ቁርባን አቅርቡ
29የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለእያንዳንዳቸው ሰባት ጠቦቶች አቅርቡ፣
30ደግሞም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአታችሁ ማስተሰርያ አቅርቡ፡፡
31ነውር የሌለባቸውን እነዚያን እንስሳት ከመጠጥ ቁርባናቸው ጋር ስታቀርቡ ይህ ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ መሆን አለበት፡፡’”